Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እርሱም፦ ማን ነሽ? አለ። እርስዋም፦ እኔ ባሪያህ ሩት ነኝ፣ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባሪያህ ላይ ዘርጋ አለችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሱም፣ “አንቺ ማነሽ?” ሲል ጠየቀ። እርሷም፣ “እኔ አገልጋይህ ሩት ነኝ፤ መቤዠት የሚገባህ ቅርብ የሥጋ ዘመድ አንተ ነህና ልብስህን ጣል አድርግብኝ” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሱም፦ “ማን ነሽ?” አለ። እርሷም፦ “እኔ ባርያህ ሩት ነኝ፥ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባርያህ ላይ ጣል አለችው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አንቺ ማን ነሽ?” ብሎም ጠየቃት። እርስዋም “ጌታዬ ሆይ! አገልጋይህ እኔ ሩት ነኝ፤ አንተ የቅርብ ዘመድ ስለ ሆንክ ለእኔ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት አለብህ፤ ስለዚህ ልብስህን ባገልጋይህ ላይ ጣል አለችው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርሱም “ማን ነሽ?” አለ። እርስዋም “እኔ ባሪያህ ሩት ነኝ፤ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባሪያህ ላይ ዘርጋ፤” አለችው።

参见章节 复制




ሩት 3:9
10 交叉引用  

በአ​ንቺ ዘንድ በአ​ለ​ፍ​ሁና በአ​የ​ሁሽ ጊዜ፥ እነሆ ጊዜሽ እንደ ደረሰ፥ በአ​ን​ቺም የሚ​ያ​ድሩ ሰዎች ጊዜ እንደ ደረሰ አየሁ። እጆ​ችን በላ​ይሽ ዘረ​ጋሁ፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ሽ​ንም ከደ​ንሁ፤ ማል​ሁ​ል​ሽም፤ ከአ​ን​ቺም ጋራ ቃል ኪዳን ገባሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ቺም ለእኔ ሆንሽ።


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


ኑኃሚንም ምራትዋን፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ፦ ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው አለቻት።


ቦዔዝም አላት፦ ልጄ ሆይ፥ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፣ ባለጠጋም ድሀም ብለሽ ጐበዛዝትን አልተከተልሽምና ከፊተኛው ይልቅ በመጨረሻው ጊዜ ቸርነት አድርገሻል።


የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፣ ነገር ግን ከእኔ የቀረበ ዘመድ አለ።


መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፥ ዘወርም አለ፣ እነሆም፥ አንዲት ሴት በእግርጌው ተኝታ ነበረች።


እኔም በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት እንድትገዛው አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ። መቤዠት ብትወድድ ተቤዥው፣ መቤዥት ባትወድድ ግን ከአንተ በቀር ሌላ ወራሽ የለምና፥ እኔም ከእንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ አለው። እርሱም፦ እቤዥዋለሁ አለው።


የቅርብ ዘመዱም፦ የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፣ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው አለ።


ተነ​ሥ​ታም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ወድቃ ሰገ​ደ​ችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረ​ድህ የጌ​ታ​ዬን ሎሌ​ዎች እግር አጥብ ዘንድ አገ​ል​ጋይ ነኝ” አለች።


跟着我们:

广告


广告