Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አማትዋም ኑኃሚን አለቻት፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈልግልሽምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ ዐማቷ ኑኃሚን ሩትን እንዲህ አለቻት፤ “ልጄ ሆይ፤ የሚመችሽን ቤት እንድፈልግልሽ አይገባኝምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አማቷም ናዖሚ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ! መልካም ይሆንልሽ ዘንድ የተመቻቸ ኑሮ የምትኖሪበትን ሁናቴ ልፈልግልሽ ይገባል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አማትዋ ናዖሚ ሩትን እንዲህ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ! መልካም ይሆንልሽ ዘንድ የተመቻቸ ኑሮ የምትኖሪበትን ሁናቴ ልፈልግልሽ ይገባል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አማትዋም ኑኃሚን አለቻት “ልጄ ሆይ! መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈልግልሽምን?

参见章节 复制




ሩት 3:1
10 交叉引用  

ነገር ግን በጎ ነገር በተ​ደ​ረ​ገ​ልህ ጊዜ እኔን ዐስ​በኝ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አድ​ር​ግ​ልኝ፤ ስለ እኔም ለፈ​ር​ዖን አሳ​ስ​በህ ከዚህ እስር ቤት አው​ጣኝ፤


ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉ​ኝም።


በሸ​መ​ገለ ጊዜ ስለ ድን​ግ​ል​ናው እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር የሚ​ያ​ስብ ሰው ቢኖር እን​ዲህ ሊሆን ይገ​ባል፤ የወ​ደ​ደ​ውን ያድ​ርግ፤ ቢያ​ገ​ባም ኀጢ​አት የለ​በ​ትም።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”


እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤


ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።


እግዚአብሔር በየባላችሁ ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ አለቻቸው። ሳመቻቸውም፣ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ።


ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፣ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር።


አሁንም ከገረዶቹ ጋር የነበርሽበት ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፥ እርሱ በዛሬ ሌሊት በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል።


跟着我们:

广告


广告