Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፣ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለዚህ የገብሱና የስንዴው አዝመራ ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ፣ ሩት የቦዔዝን ሴቶች ሠራተኞች ተጠግታ ቃረመች፤ ከዐማቷም ጋራ ኖረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝ ሠራተኞች አጠገብ እየቃረመች ቈየች፥ ከአማቷም ሳትለይ አብራ ተቀመጠች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለዚህ ሩት የገብሱና የስንዴው መከር ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ በቦዔዝ ገረዶች አጠገብ እየቃረመች ቈየች፤ ከዐማትዋም ሳትለይ አብራ ተቀመጠች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፤ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር።

参见章节 复制




ሩት 2:23
11 交叉引用  

ተል​ባ​ውና ገብሱ ተመታ፤ ገብሱ አሽቶ፥ ተል​ባ​ውም አፍ​ርቶ ነበ​ርና።


ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤ የማይሰማ ልጅ ግን ይጠፋል።


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።


ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፤


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ክፉ ነገር መል​ካም ጠባ​ይን ያበ​ላ​ሻ​ልና።


“ሰባት ሳም​ን​ትም ትቈ​ጥ​ራ​ለህ፤ መከ​ሩን ማጨድ ከም​ት​ጀ​ም​ር​በት ቀን ጀምሮ ሰባት ሳም​ንት መቍ​ጠር ትጀ​ም​ራ​ለህ።


ኑኃሚንም ከእርስዋም ጋር ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ሞዓባዊቱ ምራትዋ ሩት ተመለሱ። የገብስም መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ።


ኑኃሚንም ምራትዋን ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው አለቻት።


አማትዋም ኑኃሚን አለቻት፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈልግልሽምን?


跟着我们:

广告


广告