Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አሁን ግን ታስ​ረ​ን​በት ከነ​በ​ረው ከኦ​ሪት ሕግ ነፃ ወጥ​ተ​ናል፤ ስለ​ዚህ በብ​ሉይ መጽ​ሐፍ ሳይ​ሆን በአ​ዲሱ መን​ፈ​ሳዊ ሕይ​ወት እን​ገ​ዛ​ለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አሁን ግን ቀድሞ ጠፍሮ አስሮን ለነበረው ሞተን፣ ከሕግ ነጻ ወጥተናል፤ ይህም አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ አዲስ በሆነው በመንፈስ መንገድ እንድናገለግል ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አሁን ግን ለእርሱ ታስረን ከነበርንበት በመሞት ከሕግ ተፈትተናል፤ ስለዚህም በአሮጌው በፊደል ሳይሆን በአዲስ በመንፈስ ኑሮ እናገለግላለን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አሁን ግን አስሮን ከነበረው ሕግ በሞት የመለየት ያኽል ስለ ተለየን ከሕግ እስራት ነጻ ወጥተናል፤ ስለዚህ ከእንግዲህ የምናገለግለው በአዲሱ መንፈሳዊ መመሪያ እንጂ አስቀድሞ በተጻፈው በአሮጌው የሕግ መመሪያ አይደለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።

参见章节 复制




ሮሜ 7:6
24 交叉引用  

ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም አዲስ መን​ፈስ አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ ከሥ​ጋ​ቸ​ውም ውስጥ የድ​ን​ጋ​ዩን ልብ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤


አዲስ ልብ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ የድ​ን​ጋ​ዩ​ንም ልብ ከሥ​ጋ​ችሁ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ባለ​ማ​ቋ​ረጥ በም​ጸ​ል​የው ጸሎት እን​ደ​ማ​ስ​ባ​ችሁ ልጁ በአ​ስ​ተ​ማ​ረው ወን​ጌል በፍ​ጹም ልቡ​ናዬ የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


ይህን ዓለም አት​ም​ሰሉ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም አድሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን መል​ካ​ሙ​ንና እው​ነ​ቱን፥ ፍጹ​ሙ​ንም መር​ምሩ።


እን​ዲሁ እና​ን​ተም ራሳ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት ምው​ታን አድ​ርጉ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ዋን ሁኑ።


ስለ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ድካም በሰው ልማድ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አ​ትና ለር​ኵ​ሰት፥ ለዐ​መ​ፃም እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለጽ​ድ​ቅና ለቅ​ድ​ስና አስ​ገዙ።


ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችን የተ​ለ​የን እኛ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ዳግ​መኛ በእ​ር​ስዋ ጸን​ተን መኖር እን​ች​ላ​ለን?


ዛሬ ግን ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጣ​ችሁ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፤ ለቅ​ድ​ስ​ናም ፍሬን አፈ​ራ​ችሁ፤ ፍጻ​ሜው ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።


በሞ​ቱም እን​መ​ስ​ለው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር በጥ​ም​ቀት ተቀ​በ​ርን፤ እርሱ ክር​ስ​ቶስ በአ​ባቱ ጌት​ነት ከሙ​ታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐ​ዲስ ሕይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! ሕግን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ውሉ እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ሰው በሕ​ይ​ወት ባለ​በት ሁሉ ሕግ እን​ዲ​ገ​ዛው አታ​ው​ቁ​ምን?


ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ከእ​ርሱ ጋር በሕግ የታ​ሰ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚ​ስ​ት​ነት ታስ​ራ​በት ከኖ​ረ​ችው ሕግ የተ​ፈ​ታች ናት።


ወን​ድ​ሞች ሆይ! እና​ንተ እን​ዲሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል ስለ ሆና​ችሁ ከኦ​ሪት ተለ​ይ​ታ​ች​ኋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍሬ እን​ድ​ታ​ፈሩ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ለተ​ነ​ሣው ለዳ​ግ​ማዊ አዳም ሆና​ች​ኋል።


በመ​ን​ፈስ እንጂ በፊ​ደል ለማ​ይ​ሆን ለአ​ዲስ ሕግ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ገን፤ ፊደል ይገ​ድ​ላል፥ መን​ፈስ ግን ሕያው ያደ​ር​ጋል።


አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ የሆ​ነው ሁሉ አዲስ ፍጥ​ረት ነው፤ የቀ​ደ​መ​ውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ።


እኛ​ንስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እኛ የኦ​ሪ​ትን መር​ገም በመ​ሸ​ከሙ ከኦ​ሪት መር​ገም ዋጅ​ቶ​ናል፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥ​ረት መሆን ነው እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ምም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ው​ነት፥ በቅ​ን​ነ​ትና በን​ጽ​ሕና ያደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው​ነት ልበ​ሱት።


ግዙ​ራ​ንስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ን​ፈስ የም​ና​ገ​ለ​ግ​ለ​ውና የም​ና​መ​ል​ከው እኛ ነን፤ እኛም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​መ​ካ​ለን እንጂ በሥ​ጋ​ችን የም​ን​መካ አይ​ደ​ለም።


ፈጣ​ሪ​ውን ለመ​ም​ሰል በዕ​ው​ቀት የሚ​ታ​ደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው ልበ​ሱት።


跟着我们:

广告


广告