Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ነገር ግን በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለ​ውን ሌላ የኀ​ጢ​አት ሕግ እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ በል​ቡ​ና​ዬም ውስጥ ካለው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ጋር ተሰ​ል​ፈው ተዋጉ፤ በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀ​ጢ​አት ሕግም በረ​ታና ወደ እርሱ ማረ​ከኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ነገር ግን በብልቶቼ ውስጥ ለሚሠራው የኀጢአት ሕግ እኔን እስረኛ በማድረግ፣ ከአእምሮዬ ሕግ ጋራ የሚዋጋ ሌላ ሕግ በብልቶቼ ውስጥ ሲሠራ አያለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ነገር ግን ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በሰውነቴ ክፍሎች ባለ በኃጢአት ሕግ ምርኮኛ የሚያደርገኝ ሌላ ሕግ በሰውነቴ ክፍሎች አያለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ይሁን እንጂ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር እየተቃረነ በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ ለሚሠራው የኃጢአት ሕግ እስረኛ የሚያደርገኝ ሌላ የተፈጥሮ ዝንባሌ በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ መኖሩን አያለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ።

参见章节 复制




ሮሜ 7:23
16 交叉引用  

አቤቱ፥ ፈጥ​ነህ ስማኝ፥ ሰው​ነቴ አል​ቃ​ለች፤ ፊት​ህ​ንም ከእኔ አት​መ​ልስ፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም እን​ደ​ሚ​ወ​ርዱ አል​ሁን።


በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።


ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ራሳ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጉ እንጂ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት የዐ​መፅ የጦር መሣ​ሪያ አታ​ድ​ር​ጉት፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ የጦር መሣ​ሪያ አድ​ርጉ።


ስለ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ድካም በሰው ልማድ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አ​ትና ለር​ኵ​ሰት፥ ለዐ​መ​ፃም እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለጽ​ድ​ቅና ለቅ​ድ​ስና አስ​ገዙ።


የኦ​ሪት ሕግ መን​ፈ​ሳዊ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ እኔ ግን ለኀ​ጢ​አት የተ​ሸ​ጥሁ ሥጋዊ ነኝ።


መል​ካም ሥራ እን​ድ​ሠራ የፈ​ቀ​ደ​ል​ኝን ያን ሕግ እርሱ ክፉ ነገር አም​ጥ​ቶ​ብኝ አገ​ኘ​ሁት።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እኔ በልቤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እገ​ዛ​ለሁ፤ በሥ​ጋዬ ግን ለኀ​ጢ​አት ሕግ እገ​ዛ​ለሁ።


የሰ​ውን ሕግ በሠ​ራን ጊዜ ግን በኦ​ሪት ሕግ ደካ​ማ​ነት ቅጣቱ ጸና​ብን፤ ሞት​ንም አፈ​ራን።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ሰ​ጠን ሕይ​ወት የሚ​ገ​ኝ​በት የመ​ን​ፈስ ሕግ እርሱ ከኀ​ጢ​አ​ትና ከሞት ሕግ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።


ሥጋ መን​ፈስ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ መን​ፈ​ስም ሥጋ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ የም​ት​ሹ​ት​ንም እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እርስ በር​ሳ​ቸው ይጣ​ላሉ።


ገና አል​ጸ​ና​ች​ሁ​ምና ደማ​ች​ሁን ለማ​ፍ​ሰስ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ኀጢ​አ​ትን ተጋ​ደ​ሉ​ኣት፥ አሸ​ን​ፉ​ኣ​ትም፤ ተስ​ፋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን ትም​ህ​ር​ትም ውደ​ዷት።


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በአካላችሁ ክፍሎች ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?


ወዳጆች ሆይ! ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤


跟着我们:

广告


广告