Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የማ​ደ​ር​ገ​ውን አላ​ው​ቅ​ምና፤ የም​ወ​ደ​ው​ንም ያን ምንም አላ​ደ​ር​ገ​ው​ምና፤ ያንኑ የም​ጠ​ላ​ውን ብቻ እሠ​ራ​ለሁ እንጂ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የማደርገውን አላውቅም፤ ለማድረግ የምፈልገውን አላደርግም፤ ነገር ግን የምጠላውን ያን አደርጋለሁና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ምን እየሠራሁ እንደሆነ አላውቅም፤ የምፈልገውን ነገር አላደርግም፤ ነገር ግን የምጠላውን ነገር አደርጋለሁና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔ የማደርገውን አላውቅም፤ የምወደውን ነገር ማድረግ ትቼ የምጠላውን ነገር አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱን አላደርገውም።

参见章节 复制




ሮሜ 7:15
32 交叉引用  

“የማ​ይ​በ​ድ​ልም ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ህም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላ​ቶች ሀገር ቢማ​ረ​ኩም፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ንን መን​ገድ ያው​ቃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣን መን​ገድ ግን ትጠ​ፋ​ለች።


ዘመኔ እንደ ጢስ አል​ቋ​ልና፥ አጥ​ን​ቶቼም እንደ ሣር ደር​ቀ​ዋ​ልና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ልህ፥ የል​ብ​ህ​ንም መሻት ይሰ​ጥ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ በሉት፥ “ሥራህ ግሩም ነው፤ ኀይ​ልህ ብዙ ሲሆን ጠላ​ቶ​ችህ ዋሹ​ብህ።”


ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤ ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም።


እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ።


በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።


ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል።


እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሥራ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ሩ​ባ​ቸ​ውም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ናችሁ፤ እነ​ርሱ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውን እና​ንተ ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና።


እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


ፍቅ​ራ​ችሁ ያለ ግብ​ዝ​ነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎ​ው​ንም ያዙ፤ ለጽ​ድቅ አድሉ፤


እም​ነት ካለህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባመ​ን​ኸው እም​ነት ራስ​ህን አጽና፤ ባገ​ኘው አእ​ም​ሮም ራሱን የሚ​ዘ​ልፍ ብፁዕ ነው።


የማ​ል​ወ​ደ​ውን የም​ሠራ ከሆ​ንሁ ግን ያ የኦ​ሪት ሕግ መሠ​ራት ለበጎ እንደ ሆነ ምስ​ክሩ እኔ ነኝ።


ሥጋ መን​ፈስ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ መን​ፈ​ስም ሥጋ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ የም​ት​ሹ​ት​ንም እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እርስ በር​ሳ​ቸው ይጣ​ላሉ።


ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።


“ጽድ​ቅን ወደ​ድህ፤ ዐመ​ፃ​ንም ጠላህ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ንተ ካሉት ይልቅ የሚ​በ​ልጥ የደ​ስታ ዘይ​ትን ቀባህ።”


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።


跟着我们:

广告


广告