Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በሞ​ቱም እን​መ​ስ​ለው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር በጥ​ም​ቀት ተቀ​በ​ርን፤ እርሱ ክር​ስ​ቶስ በአ​ባቱ ጌት​ነት ከሙ​ታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐ​ዲስ ሕይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ፣ እኛም እንዲሁ በአዲስ ሕይወት እንድንኖር በጥምቀት ሞተን ከርሱ ጋራ ተቀብረናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ በአብ ክብር ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንኖር፥ በጥምቀት አማካኝነት በሞት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በጥምቀት ከእርሱ ጋር በተቀበርን ጊዜ የእርሱም ሞት ተካፋዮች ሆነናል፤ ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ እኛም በአዲስ ሕይወት እንኖራለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።

参见章节 复制




ሮሜ 6:4
33 交叉引用  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ብታ​ም​ናስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ታያ​ለሽ አላ​ል​ሁ​ሽም ነበ​ርን?” አላት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን የሞ​ትን ማሰ​ሪያ ፈቶ ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ሞት እር​ሱን ሊይ​ዘው አይ​ች​ል​ምና።


እር​ሱን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ሁላ​ችን ምስ​ክ​ሮቹ ነን።


ስለ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ድካም በሰው ልማድ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አ​ትና ለር​ኵ​ሰት፥ ለዐ​መ​ፃም እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለጽ​ድ​ቅና ለቅ​ድ​ስና አስ​ገዙ።


ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ጠ​መ​ቅን እኛ ሁላ​ችን በሞቱ እንደ ተጠ​መ​ቅን ሁላ​ችሁ ይህን ዕወቁ።


ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ት​ንም ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ደ​ም​ን​ኖር እና​ም​ና​ለን።


ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ዳግ​መ​ኛም እን​ደ​ማ​ይ​ሞት፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ሞት እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ዛው እና​ው​ቃ​ለን።


አሁን ግን ታስ​ረ​ን​በት ከነ​በ​ረው ከኦ​ሪት ሕግ ነፃ ወጥ​ተ​ናል፤ ስለ​ዚህ በብ​ሉይ መጽ​ሐፍ ሳይ​ሆን በአ​ዲሱ መን​ፈ​ሳዊ ሕይ​ወት እን​ገ​ዛ​ለን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኛ​ንም በከ​ሃ​ሊ​ነቱ ያስ​ነ​ሣ​ናል።


በድ​ካም ተሰ​ቅ​ሎ​አ​ልና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይል ሕያው ነውና፤ እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ደ​ክ​ማ​ለ​ንና፤ ነገር ግን ስለ እና​ንተ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።


አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ የሆ​ነው ሁሉ አዲስ ፍጥ​ረት ነው፤ የቀ​ደ​መ​ውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ።


እን​ግ​ዲህ በል​ባ​ቸው ከንቱ አሳብ እን​ደ​ሚ​ኖሩ እንደ አሕ​ዛብ እን​ዳ​ት​ኖሩ ይህን እላ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።


ቀድሞ ጨለማ ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ዛሬ ግን በጌ​ታ​ችን ብር​ሃን ሆና​ች​ኋል። እን​ግ​ዲ​ህስ እንደ ብር​ሃን ልጆች ተመ​ላ​ለሱ።


ፈጣ​ሪ​ውን ለመ​ም​ሰል በዕ​ው​ቀት የሚ​ታ​ደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው ልበ​ሱት።


ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፤ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤


በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።


跟着我们:

广告


广告