Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አት አት​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ታ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ገብ​ታ​ች​ኋ​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆናችሁ፣ ኀጢአት አይገዛችሁምና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆናችሁ ኃጢአት አይገዛችሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አሁን እናንተ የምትኖሩት ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆነ ኃጢአት ሊገዛችሁ አይገባም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።

参见章节 复制




ሮሜ 6:14
25 交叉引用  

በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ከአ​ንተ ይወ​ጣል፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም፥ ወደ አባ​ቱም ርስት ይመ​ለ​ሳል።


ተመልሶ ይምረናል፥ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።


ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።


ወልድ አር​ነት ካወ​ጣ​ችሁ በእ​ው​ነት አር​ነት የወ​ጣ​ችሁ ናችሁ።


በጸጋ ከጸ​ደቁ ግን በሥ​ራ​ቸው አይ​ደ​ለማ፤ በሥ​ራም የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ ጸጋ ጸጋ አይ​ባ​ልም።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ የሰ​ጠው ተስፋ የታ​መነ ይሆን ዘንድ፥ የሚ​ጸ​ድቁ በእ​ም​ነት እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ፈ​ጸም ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ ያውቁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን በእ​ም​ነት አደ​ረገ።


የአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት ሞትን ካነ​ገ​ሠ​ችው በአ​ንድ ሰው በደ​ልም ሞት ከገ​ዛን፥ የአ​ንዱ ሰው የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጸ​ጋው ብዛ​ትና የጽ​ድቁ ስጦታ እን​ዴት እጅግ ያጸ​ድ​ቀን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ት​ንስ እን​ዴት ያበ​ዛ​ልን ይሆን?


እን​ግ​ዲህ በአ​ንዱ ሰው በደል ዓለም ሁሉ እንደ ተፈ​ረ​ደ​በት፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንዱ ሰው ጽድቅ ሰው ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል።


በዚህ በሚ​ሞት ሰው​ነ​ታ​ችሁ ኀጢ​አ​ትን አታ​ን​ግ​ሡ​አት፤ ለም​ኞ​ቱም እሽ አት​በ​ሉት።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ተን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ስለ ገባን ኀጢ​አት እን​ሥ​ራን? አይ​ደ​ለም።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ አሁ​ንም በሥ​ጋ​ችን ሳለን በሥጋ ፈቃድ እን​ኖር ዘንድ አይ​ገ​ባም።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ሰ​ጠን ሕይ​ወት የሚ​ገ​ኝ​በት የመ​ን​ፈስ ሕግ እርሱ ከኀ​ጢ​አ​ትና ከሞት ሕግ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።


እም​ነት ሳይ​መጣ ኦሪት ጠበ​ቀ​ችን፤ ወደ​ሚ​መ​ጣ​ውም እም​ነት መራ​ችን።


በኦ​ሪት ሕግ እን​ኑር ትላ​ላ​ች​ሁን? ኦሪ​ትን አት​ሰ​ሙ​አ​ት​ምን?


የመ​ን​ፈ​ስን ፈቃድ የም​ት​ከ​ተሉ ከሆ​ና​ችሁ፥ ከኦ​ሪት ወጥ​ታ​ች​ኋል።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ከእ​ነ​ዚያ ዘመ​ናት በኋላ ለቤተ እስ​ራ​ኤል የም​ገ​ባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በል​ባ​ቸው አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ በሕ​ሊ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


跟着我们:

广告


广告