Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 6:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እን​ዲሁ እና​ን​ተም ራሳ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት ምው​ታን አድ​ርጉ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ዋን ሁኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንደዚሁም ለኀጢአት እንደ ሞታችሁ፣ ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቍጠሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲሁም ደግሞ እናንተ በአንድ በኩል በእርግጥ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ በሌላ በኩል ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንግዲህ እናንተ የመሞት ያኽል ከኃጢአት እንደ ተለያችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ግን ለእግዚአብሔር በሕይወት እንደምትኖሩ አስቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቍኦጠሩ።

参见章节 复制




ሮሜ 6:11
21 交叉引用  

ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን። በቆ​ሮ​ን​ቶስ ተጽፋ ለክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያን በም​ት​ላ​ላ​ከው በፌ​ቤን እጅ ወደ ሮሜ ሰዎች የተ​ላ​ከ​ችው መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።


እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ከጸ​ደ​ቅን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምን እና​ገ​ና​ለን።


የሞተ አንድ ጊዜ ሞተ፤ በሞ​ቱም ኀጢ​አ​ትን ሻራት፤ የተ​ነ​ሣም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተነሣ።


ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ራሳ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጉ እንጂ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት የዐ​መፅ የጦር መሣ​ሪያ አታ​ድ​ር​ጉት፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ የጦር መሣ​ሪያ አድ​ርጉ።


ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችን የተ​ለ​የን እኛ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ዳግ​መኛ በእ​ር​ስዋ ጸን​ተን መኖር እን​ች​ላ​ለን?


የኀ​ጢ​አት ትር​ፍዋ ሞት ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።


ወን​ድ​ሞች ሆይ! እና​ንተ እን​ዲሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል ስለ ሆና​ችሁ ከኦ​ሪት ተለ​ይ​ታ​ች​ኋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍሬ እን​ድ​ታ​ፈሩ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ለተ​ነ​ሣው ለዳ​ግ​ማዊ አዳም ሆና​ች​ኋል።


አሁን ግን ታስ​ረ​ን​በት ከነ​በ​ረው ከኦ​ሪት ሕግ ነፃ ወጥ​ተ​ናል፤ ስለ​ዚህ በብ​ሉይ መጽ​ሐፍ ሳይ​ሆን በአ​ዲሱ መን​ፈ​ሳዊ ሕይ​ወት እን​ገ​ዛ​ለን።


ነገር ግን የዚህ ዓለም መከራ ለእና ሊገ​ለጥ ከአ​ለው ክብር ጋር እን​ደ​ማ​ይ​ተ​ካ​ከል ዐስቡ።


በዋጋ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ጋ​ችሁ አክ​ብ​ሩት።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይቅር ስላ​ለን የጸ​ጋ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነት ብዛት በሚ​መ​ጣው ዓለም ይገ​ልጥ ዘንድ፥


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጽ​ድ​ቅን ፍሬ ትሞሉ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤


ሁሉ የሚ​ገ​ኝ​ባት፥ ከል​ቡ​ናና ከአ​ሳብ ሁሉ በላይ የም​ት​ሆን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ልባ​ች​ሁ​ንና አሳ​ባ​ች​ሁን ታጽ​ናው።


ከዚህ ዓለም ኑሮ ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ታ​ችሁ እን​ደ​ገና በዓ​ለም እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች እን​ዴት ትሠ​ራ​ላ​ችሁ?


በቃ​ልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም አድ​ርጉ፤ ስለ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።


ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告