Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አንተ ሰው ሆይ፥ እው​ነት ለሚ​ፈ​ር​ደው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ? በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ጠ​ላ​ውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠ​ራ​ኸው በራ​ስህ የም​ት​ፈ​ርድ አይ​ደ​ለ​ምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠ​ራ​ዋ​ለ​ህና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ስለዚህ አንተ በሌላው ላይ የምትፈርድ፣ የምታመካኝበት የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ፣ ራስህን ትኰንናለህ፤ ፈራጅ የሆንኸው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና።

参见章节 复制




ሮሜ 2:1
20 交叉引用  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው።


ጌታ​ውም እን​ዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገ​ል​ጋይ፥ እኔ ያላ​ስ​ቀ​መ​ጥ​ሁ​ትን የም​ወ​ስድ፥ ያል​ዘ​ራ​ሁ​ትን የማ​ጭድ፥ ያል​በ​ተ​ን​ሁ​ት​ንም የም​ሰ​በ​ስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለ​ህን? እንደ ቃልህ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ።


አት​ፍ​ረዱ፥ አይ​ፈ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁ​ምም፤ አት​በ​ድሉ፥ አይ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምም፤ ይቅር በሉ፥ ይቅ​ርም ይሉ​አ​ች​ኋል።


እም​ነት ካለህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባመ​ን​ኸው እም​ነት ራስ​ህን አጽና፤ ባገ​ኘው አእ​ም​ሮም ራሱን የሚ​ዘ​ልፍ ብፁዕ ነው።


ይህም እን​ደ​ዚህ በሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች ላይ ቅጣት የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርዱ እው​ነት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።


አንተ ሰው ሆይ፥ በሌላ ላይ አይ​ተህ የም​ት​ጠ​ላ​ው​ንና የም​ት​ነ​ቅ​ፈ​ውን ያን አንተ ራስህ የም​ት​ሠ​ራው ከሆነ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እን​ደ​ም​ታ​መ​ልጥ ታስ​ባ​ለ​ህን?


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ከእ​ነ​ርሱ እን​በ​ል​ጣ​ለን? አይ​ደ​ለም፤ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንም፥ አረ​ማ​ዊ​ንም እነሆ፥ አስ​ቀ​ድ​መን ነቅ​ፈ​ና​ቸ​ዋል፤ ሁሉም ስተ​ዋ​ልና።


ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን?


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


ሚስ​ትም ባል​ዋን ታድ​ነው እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምና፤ ባልም ሚስ​ቱን ያድ​ናት እንደ ሆነ አያ​ው​ቅ​ምና።


አንተ ከንቱ ሰው! እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?


ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም።


跟着我们:

广告


广告