Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሁላ​ችን አንድ ሆነን በአ​ንድ አፍ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ይኸውም በአንድ ልብና በአንድ አፍ ሆናችሁ፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት ታከብሩ ዘንድ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ይኸውም በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት፥ እንድታከብሩ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እንዲሁም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር በአንድ ልብና በአንድ ቃል እንድታከብሩት ያድርጋችሁ።

参见章节 复制




ሮሜ 15:6
14 交叉引用  

በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ን​ኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላ​ረ​ግ​ሁ​ምና፤ ነገር ግን ወደ ወን​ድ​ሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አም​ላኬ፥ ወደ አም​ላ​ካ​ች​ሁም አር​ጋ​ለሁ አለ ብለሽ ንገ​ሪ​አ​ቸው” አላት።


ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ በአ​ን​ድ​ነት ቃላ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ አድ​ር​ገው እን​ዲህ አሉ፥ “ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ የፈ​ጠ​ርህ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥


ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም።


የም​ሕ​ረት አባት፥ የመ​ጽ​ና​ና​ትም ሁሉ አም​ላክ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ የሆነ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሰት እን​ደ​ማ​ል​ና​ገር ያው​ቃል።


ይኸ​ውም የክ​ብር ባለ​ቤት የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ ዕው​ቀ​ቱ​ንም ይገ​ል​ጽ​ላ​ችሁ ዘንድ፥


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዘወ​ትር ስለ እና​ንተ እና​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለን።


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።


መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告