ሮሜ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ወንድሞች ሆይ፥ እኔም በጎ ምግባርን ሁሉ እንደምትፈጽሙ እታመንባችኋለሁ፤ እናንተ ፍጹም ዕውቀትን የተመላችሁ ናችሁ፤ ባልንጀሮቻችሁንም ልታስተምሩአቸው ትችላላችሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ወንድሞቼ ሆይ፤ እናንተ ራሳችሁ በበጎነት የተሞላችሁ፣ በዕውቀትም ሁሉ የተሞላችሁና አንዱ ሌላውን ለመምከር ችሎታ ያላችሁ መሆናችሁን እኔ ራሴ ርግጠኛ ሆኛለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ወንድሞቼ ሆይ! እኔም ራሴ ስለ እናንተ በበጎነት ራሳችሁ እንደ ተሞላችሁ፥ እውቀትም ሁሉ እንደ ሞላባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ደግሞ ልትወቃቀሱ እንደምትችሉ ተረድቼአለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ወንድሞቼ ሆይ! በደግነት የተሞላችሁ፥ በዕውቀት የበለጸጋችሁና እያንዳንዳችሁም ሌላውን ለመምከር የምትችሉ መሆናችሁን ተረድቼአለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እኔም ራሴ ደግሞ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በበጎነት ራሳችሁ እንደ ተሞላችሁ፥ እውቀትም ሁሉ እንደ ሞላባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ደግሞ ልትገሠጹ እንዲቻላችሁ ስለ እናንተ ተረድቼአለሁ። 参见章节 |