Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 1:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የሚ​ገ​ባ​ውን ትተው ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ሠሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር አሳፋሪ ለሆነ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም እንኳ ለባሕርያቸው የሚገባውን ግንኙነት ባሕርያቸው ላልሆነው ግንኙነት ለወጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ለሚያዋርድ ፍትወት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ተፈጥሮአዊውን ግንኙነት ተፈጥሮአዊ ባልሆነ ግንኙነት ለወጡ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሰዎች ይህን በማድረጋቸው ምክንያት እግዚአብሔር ለማይገባ አስነዋሪ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸው እንኳ የተለመደውን ተፈጥሮአዊ ግንኙነት ባልተለመደ ግንኙነት ለወጡት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤

参见章节 复制




ሮሜ 1:26
14 交叉引用  

ሎጥ​ንም ጠር​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “በሌ​ሊት ወደ አንተ የገ​ቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እና​ው​ቃ​ቸው ዘንድ ወደ እኛ አው​ጣ​ቸው።”


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ቸው ሥጋ​ቸ​ውን ሊያ​ዋ​ርዱ በል​ባ​ቸው ፍት​ወት ወደ ርኵ​ሰት አሳ​ልፎ ተዋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


ዐመ​ፀ​ኞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እን​ደ​ማ​ይ​ወ​ርሱ አታ​ው​ቁ​ምን? አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ሴሰ​ኞች፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ወይም አመ​ን​ዝ​ራ​ዎች፥ ወይም ቀላ​ጮች፥ ወይም በወ​ንድ ላይ ዝሙ​ትን የሚ​ሠሩ፥ የሚ​ሠ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ቢሆኑ፤


ተስፋ የቈ​ረጡ ናቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ለጕ​ስ​ቍ​ልና፥ ለር​ኵ​ሰ​ትና ለመ​ዳ​ራት አሳ​ል​ፈው ሰጡ።


በስ​ውር የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ለመ​ና​ገር የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነውና።


እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፤ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።


እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች የሆኑ የከ​ተ​ማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩ​ንም ይደ​በ​ድቡ ነበር፤ ባለ​ቤ​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገ​ባ​ውን ሰው እን​ድ​ን​ደ​ር​ስ​በት አው​ጣ​ልን” አሉት።


跟着我们:

广告


广告