Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “ጻድቅ በእ​ም​ነት ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከእ​ም​ነት ወደ እም​ነት በእ​ርሱ ይገ​ለ​ጣ​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በወንጌል የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጧልና፤ ጽድቁም ከእምነት ወደ እምነት የሆነ ነው፤ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጻድቅ በእምነት ሕይወትን ያገኛል ተብሎ ተጽፎአል፤ የእግዚአብሔር ጽድቅም በሥራ ስለ ታየ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ሰው የሚጸድቀው በእምነት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።

参见章节 复制




ሮሜ 1:17
15 交叉引用  

በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እው​ነ​ት​ንም ለማ​ድ​ረግ ፍር​ዴን ቢጠ​ብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፣ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።


ሙሴም የና​ሱን እባብ ሠርቶ በዓ​ላማ ላይ ሰቀለ፤ እባ​ብም የነ​ደ​ፈ​ችው ሁሉ የና​ሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።


በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ አያ​ው​ቁ​አ​ት​ምና በራ​ሳ​ቸ​ውም ጽድቅ ጸን​ተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ግን መገ​ዛት ተሳ​ና​ቸው።


አሁን ግን በኦ​ሪ​ትና በነ​ቢ​ያት የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ያለ ኦሪት ተገ​ለ​ጠች።


የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይጸ​ድ​ቃሉ።


የማ​ያ​ምኑ ቢኖ​ሩስ የእ​ነ​ርሱ አለ​ማ​መን ሌላ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ምን ይከ​ለ​ክ​ላ​ልን? አይ​ከ​ለ​ክ​ልም።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ጽድ​ቅን ያል​ፈ​ለ​ጉ​አት አሕ​ዛብ ስንኳ ጽድ​ቅን አገ​ኙ​አት፤ በእ​ም​ነ​ትም ጸደቁ።


ኵነ​ኔን ለም​ታ​መጣ መል​እ​ክት ብዙ ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት የጽ​ድቅ መል​እ​ክ​ትማ ምን ያህል ትከ​ብ​ርና ትመ​ሰ​ገን ይሆን?


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራ​ትስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቁ ይታ​ወ​ቃል፤ “ጻድቅ ግን በእ​ም​ነት ይድ​ናል” ተብሎ ተጽ​ፎ​አል።


በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ።


ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”


跟着我们:

广告


广告