Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጥልቁን ጕድጓድ በከፈተውም ጊዜ፣ ከውስጡ ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ያለ ጢስ ወጣ። ከጕድጓዱም በወጣው ጢስ ፀሓይና ሰማይ ጨለሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የጥልቁንም ጉድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጉድጓዱ ወጣ፤ ፀሐይና አየርም በጉድጓዱ ጢስ ጨለሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እርሱ የጥልቁን ጒድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጥልቁ ጒድጓድ ወጣ፤ ከጒድጓዱ በወጣው ጢስ ምክንያት ፀሐይና አየር ጨለሙ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጕዱ ጢስ ጨለሙ።

参见章节 复制




ራእይ 9:2
16 交叉引用  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ነበ​ል​ባል መጣ፤ የእ​ሳት መብ​ራ​ትና የሚ​ጤስ ምድ​ጃም መጣ፤ በዚ​ያም በተ​ከ​ፈ​ለው መካ​ከል አለፈ።


ወደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ ወደ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋም ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ነበ​ል​ባል ከም​ድር እንደ ምድጃ ጢስ ሲወጣ አየ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


እና​ንተ የከ​ተ​ሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እና​ን​ተም ከተ​ሞች ሆይ፥ ደን​ግጡ፥ ጩኹም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ፥ ሁላ​ች​ሁም ቀል​ጣ​ች​ኋል፤ ጢስ ከሰ​ሜን ይወ​ጣ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሩ​ምና።


ምድ​ሪ​ቱም ከፊ​ታ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ሰማ​ይም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ ፀሐ​ይና ጨረ​ቃም ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ።


የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።


በላይ በሰ​ማይ ድን​ቆ​ችን አሳ​ያ​ለሁ፤ በታች በም​ድ​ርም ደምና እሳት የጢ​ስም ጭጋግ።


በላይ በሰ​ማይ ተአ​ም​ራ​ትን፥ በታች በም​ድ​ርም ምል​ክ​ቶ​ችን፥ ደምን እሳ​ት​ንና ጢስ​ንም እሰ​ጣ​ለሁ።


የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”


አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች፤ ከስቃይም የተነሣ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፤


አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።


አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።


በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው፤ እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።


ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፤ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ።


跟着我们:

广告


广告