Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር፣ “ና!” ሲል ሰማሁ። እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ ጥቍር ፈረስ ቆሞ አየሁ፤ ተቀምጦበት የነበረውም በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “ና” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “ና!” ሲል ሰማሁ፤ እነሆ ጥቊር ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ሚዛን በእጁ ይዞ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።

参见章节 复制




ራእይ 6:5
11 交叉引用  

ከራብ የተ​ነሣ ሰው​ነ​ታ​ችን ጠወ​ለገ፤ ቍር​በ​ታ​ች​ንም እንደ ምድጃ ጠቈረ።


የም​ት​በ​ላ​ውም በሚ​ዛን በየ​ቀኑ ሃያ ሃያ ሰቅል ይሁን፤ በየ​ጊ​ዜው ትበ​ላ​ዋ​ለህ።


ደግ​ሞም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እን​ጀራ በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በች​ግር እያሉ እን​ጀ​ራን በሚ​ዛን ይበ​ላሉ፥ እየ​ደ​ነ​ገ​ጡም ውኃን በልክ ይጠ​ጣሉ፤


በእ​ህል ረሃብ ባስ​ጨ​ነ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እን​ጀራ በአ​ንድ ምጣድ ይጋ​ግ​ራሉ፤ በሚ​ዛ​ንም መዝ​ነው እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ይመ​ል​ሱ​ላ​ች​ኋል፤ በበ​ላ​ች​ሁም ጊዜ አት​ጠ​ግ​ቡም።


በፊተኛው ሰረገላ መጋላ ፈረሶች፥ በሁለተኛውም ሰረገላ ዱሪ ፈረሶች ነበሩ፥


ዱሪ ፈረሶች ያሉበት ወደ ሰሜን ይወጣል፣ አምባላዮቹም ከእነርሱ በኋላ ይወጣሉ፥ ቅጥልጣሎቹም ወደ ደቡብ ይወጣሉ አለኝ።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告