Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ አንድ ነጭ ፈረስ ነበረ፤ በፈረሱም ላይ፣ “ታማኝና እውነተኛ” የሚባል ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ፥ ነጭ ፈረስም አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ የሚባል ነው፤ እርሱ በትክክል ይፈርዳል፤ ይዋጋልም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።

参见章节 复制




ራእይ 19:11
28 交叉引用  

እነሆ፥ እው​ነ​ትን ወደ​ድህ፤ የማ​ይ​ነ​ገር ስውር ጥበ​ብ​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ኸኝ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራራ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነውና።


ወደ ደጆቹ በመ​ገ​ዛት፥ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ቹም በም​ስ​ጋና ግቡ፤ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም አክ​ብሩ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጦር​ነ​ትን ያጠ​ፋል፤ ስሙም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤


እነሆ፥ ጻድቅ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ መሳ​ፍ​ን​ትም በፍ​ርድ ይገ​ዛሉ።


የሚ​ና​ገሩ ከሆነ ከጥ​ንት ጀምሮ ይህን ምስ​ክ​ር​ነት ያደ​ረገ ማን እንደ ሆነ በአ​ን​ድ​ነት ያውቁ ዘንድ ይቅ​ረቡ። ያሳ​የ​ሁም የተ​ና​ገ​ር​ሁም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አም​ላ​ክና መድ​ኀ​ኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


በዚ​ያም ዘመን በዚ​ያም ጊዜ ለዳ​ዊት የጽ​ድ​ቅን ቍጥ​ቋጥ አበ​ቅ​ል​ለ​ታ​ለሁ፤ እር​ሱም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን በም​ድር ያደ​ር​ጋል።


በሠ​ላ​ሳ​ኛው ዓመት በአ​ራ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በኮ​ቦር ወንዝ በም​ር​ኮ​ኞች መካ​ከል ሳለሁ ሰማ​ያት ተከ​ፈቱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ራእይ አየሁ።


እነሆም፥ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፣ በስተ ኋላውም መጋላና ሐመር አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “በበ​ለስ ዛፍ ሥር አየ​ሁህ ስለ አል​ሁህ አመ​ን​ህን? ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ታያ​ለህ” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።


የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።


“በሎዲቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦


ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።


አየሁም፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድልም እየነሣ ወጣ፤ ድል ለመንሣት።


跟着我们:

广告


广告