Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሥቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል። ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ ወይም የስሙንም ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሥቃያቸውም ጢስ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነርሱን ከሚያሠቃየው እሳት የሚወጣው ጢስ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት ያደረጉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፥ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

参见章节 复制




ራእይ 14:11
30 交叉引用  

ወደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ ወደ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋም ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ነበ​ል​ባል ከም​ድር እንደ ምድጃ ጢስ ሲወጣ አየ።


ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለ​ምም ይነ​ግ​ሣል።


በጽ​ዮን ያሉ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ፈሩ፤ መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ዝን​ጉ​ዎ​ችን ያዘ፤ እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሀገ​ር​ንስ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው?


ጢሱም ወደ​ላይ ይወ​ጣል፤ ከት​ው​ልድ እስከ ትው​ል​ድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖ​ራ​ለች፤ ለብዙ ዘመ​ና​ትም ትጠ​ፋ​ለች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ርዱ ቀን፥ ስለ ጽዮ​ንም ፍርድ የብ​ድ​ራት ዓመት ነውና።


“ኃጥ​ኣን ግን እን​ዲህ ይገ​ለ​በ​ጣሉ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አያ​ገ​ኙም።


በላይ በሰ​ማይ ድን​ቆ​ችን አሳ​ያ​ለሁ፤ በታች በም​ድ​ርም ደምና እሳት የጢ​ስም ጭጋግ።


እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


በእ​ነ​ዚ​ያም አሕ​ዛብ መካ​ከል ዕረ​ፍት አታ​ገ​ኝም፤ ለእ​ግ​ር​ህም ጫማ ማረ​ፊያ አይ​ሆ​ንም፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተን​ቀ​ጥ​ቃጭ ልብ ፥ ፈዛዛ ዐይን፥ ደካ​ማም ነፍስ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።


ስለ ልጁ ግን፥ “ጌታ ሆይ፥ ዙፋ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በት​ርም የጽ​ድቅ በትር ነው” አለ።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት፤ ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።


የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።


የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል።


ሦስተኛም መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥


የመቃጠልዋንም ጢስ ባዩ ጊዜ “ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች?” እያሉ ጮኹ።


ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮሁ እያሉ ያለቅሳሉ፤


ደግመውም “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል፤” አሉ።


ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።


“አሜን በረከትና ገናናነት ጥበብም ምስጋናም ክብርም ኀይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን! አሜን።” አሉ።


跟着我们:

广告


广告