Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይህም የሆነው የአውሬው ምልክት፣ ይኸውም ስሙ ወይም የስሙ ቍጥር የሌለው ማንም ሰው ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ እንዳይችል ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሰው ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችልም ያደርጋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በዚህ ዐይነት የአውሬውን ስም የሚያሳይ ምልክት ወይም የስሙ ቊጥር የሌለው ማንም ሰው መግዛትም ሆነ መሸጥ አይችልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።

参见章节 复制




ራእይ 13:17
11 交叉引用  

እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ የሚ​ያ​ደ​ክ​መኝ አይ​ኑር፤ እኔ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን መከራ በሥ​ጋዬ እሸ​ከ​ማ​ለሁ።


ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥


ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፤ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።


የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”


ሦስተኛም መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥


በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፤ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።


በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት” ተብሎ ተጻፈ።


ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።


ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።


ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።


“የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ፤” አላቸው።


跟着我们:

广告


广告