Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 98:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ታላቅ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታ ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር አዳኝነቱ እንዲታወቅ አደረገ፤ ጽድቁንም ለአሕዛብ ገለጠ።

参见章节 复制




መዝሙር 98:2
23 交叉引用  

በእ​ው​ነ​ትህ ምራኝ፤ አስ​ተ​ም​ረ​ኝም፤ አንተ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ነህና፥ ዘወ​ት​ርም አን​ተን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና።


ጽድ​ቄን አመ​ጣ​ኋት፤ ከእኔ ዘንድ የም​ት​ገኝ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም አላ​ዘ​ገ​ይም፤ ከጽ​ዮን ለክ​ብር እን​ዲ​ሆን መድ​ኀ​ኒ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጥ​ቻ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ነገ​ዶች እን​ደ​ገና እን​ድ​ታ​ስ​ነሣ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ወደ አባ​ቶች ቃል ኪዳን እን​ድ​ት​መ​ልስ ባር​ያዬ ትሆን ዘንድ ለአ​ንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ይላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ክን​ዱን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ገል​ጦ​አል፤ በም​ድር ዳርቻ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን ያያሉ።


ሰላ​ምን የሚ​ያ​ወራ፥ መል​ካም የም​ሥ​ራ​ች​ንም የሚ​ና​ገር፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም የሚ​ያ​ወራ፥ ጽዮ​ን​ንም፥ “አም​ላ​ክሽ ነግ​ሦ​አል” የሚል ሰው እግሩ በተ​ራ​ሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።


አሕ​ዛብ ጽድ​ቅ​ሽን፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ ክብ​ር​ሽን ያያሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ በሚ​ጠ​ራ​በት በአ​ዲሱ ስም ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።


በዘ​መ​ኑም ይሁዳ ይድ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተዘ​ልሎ ይቀ​መ​ጣል፤ ይህም ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያት ኢዮ​ሴ​ዴቅ ብሎ የጠ​ራው ነው።


እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም፥ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


እንዲህም አላቸው “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።


ሰውም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ።”


“ጻድቅ በእ​ም​ነት ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከእ​ም​ነት ወደ እም​ነት በእ​ርሱ ይገ​ለ​ጣ​ልና።


ነገር ግን እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በውኑ እስ​ራ​ኤል ብቻ አል​ሰ​ሙ​ምን? መጽ​ሐፍ “ነገ​ራ​ቸው በም​ድር ሁሉ ተሰማ፤ ቃላ​ቸ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ” ብሎ የለ​ምን?


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ጽድ​ቅን ያል​ፈ​ለ​ጉ​አት አሕ​ዛብ ስንኳ ጽድ​ቅን አገ​ኙ​አት፤ በእ​ም​ነ​ትም ጸደቁ።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ።


የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤


跟着我们:

广告


广告