Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 97:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለያ​ዕ​ቆብ ይቅ​ር​ታ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት እው​ነ​ቱን አሰበ፤ የም​ድር ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን እዩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እሳት እፊት እፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ያቃጥላል።

参见章节 复制




መዝሙር 97:3
19 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐት ቅን ነው፥ ልብ​ንም ደስ ያሰ​ኛል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ብሩህ ነው፥ ዐይ​ኖ​ች​ንም ያበ​ራል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ንጹሕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይኖ​ራል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እው​ነ​ትና ቅን​ነት በአ​ን​ድ​ነት ነው።


እኔ በደ​ሌን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ር​ንም ከፍ​ሬዋ፤ ጋር ትበ​ላ​ለች፤ የተ​ራ​ሮ​ችን መሠ​ረት ታነ​ድ​ዳ​ለች።


እና​ን​ተም ቀር​ባ​ችሁ ከተ​ራ​ራው በታች ቆማ​ችሁ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም እስከ ሰማይ ድረስ በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ጨለ​ማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም ነበረ።


ያስ​ተ​ም​ርህ ዘንድ ከሰ​ማይ ድም​ፁን አሰ​ማህ፤ በም​ድ​ርም ላይ ታላ​ቁን እሳት አሳ​የህ፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ቃሉን ሰማህ።


በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለፊት ተና​ገ​ራ​ችሁ።


እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤


አም​ላ​ካ​ችን በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነውና።


ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።


በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።


跟着我们:

广告


广告