Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 91:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ያን​ጊዜ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ይበ​ዛሉ፤ ዕረ​ፍት ያላ​ቸ​ውም ሆነው ይኖ​ራሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፥ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለሚወደኝ ከጠላቶቹ እጅ አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም ስለሚያውቅ እጠብቀዋለሁ።

参见章节 复制




መዝሙር 91:14
17 交叉引用  

ከዚ​ህም በላይ ደግሞ የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ስለ ወደ​ድሁ፥ ለመ​ቅ​ደሱ ከሰ​በ​ሰ​ብ​ሁት ሁሉ ሌላ የግል ገን​ዘቤ የሚ​ሆን ወር​ቅና ብር አለ​ኝና እነሆ፥ ለአ​ም​ላኬ ቤት ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሄድ ዘንድ ከአ​ኅዋ ወንዝ ተነ​ሣን፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም እጅ በላ​ያ​ችን ነበረ፤ በመ​ን​ገ​ድም ከጠ​ላ​ትና ከሚ​ሸ​ምቅ ሰው እጅ አዳ​ነን።


አቤቱ፥ ጣል​ኸን አፈ​ረ​ስ​ኸ​ንም፤ ገረ​ፍ​ኸን፥ ይቅ​ርም አል​ኸን።


ስም​ህን የሚ​ወዱ ሁሉ በአ​ንተ ይታ​መ​ናሉ፥ አቤቱ፥ የሚ​ሹ​ህን አት​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና።


በጽ​ዮን ለሚ​ኖር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን ንገሩ፤


አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ይጠ​ፋ​ሉና፥ ዐመ​ፃ​ንም የሚ​ሠሩ ሁሉ ይበ​ተ​ና​ሉና።


እርሱ ከፍ ባለ በጽ​ኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖ​ራል፤ እን​ጀ​ራም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ውኃ​ውም የታ​መ​ነች ትሆ​ና​ለች።


በዚ​ያም ቀን አድ​ን​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው ሰዎች እጅ አል​ሰ​ጥ​ህም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አለው፥ “የሚ​ወ​ደኝ ቃሌን ይጠ​ብ​ቃል፤ አባ​ቴም ይወ​ደ​ዋል፤ ወደ እር​ሱም መጥ​ተን በእ​ርሱ ዘንድ ማደ​ሪያ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


እና​ንተ ስለ ወደ​ዳ​ች​ሁኝ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ወጣሁ ስለ አመ​ና​ች​ሁ​ብኝ እርሱ ራሱ አብ ወድ​ዷ​ች​ኋ​ልና።


ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐወ​ቃ​ች​ሁት፤ ይል​ቁ​ንም እርሱ ዐወ​ቃ​ችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደ​ዚያ ወደ ደካ​ማው፥ ወደ ድሀው ወደ​ዚህ ዓለም ጣዖት ተመ​ል​ሳ​ችሁ፥ ትገ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ዴት ፈጠ​ራን ትሻ​ላ​ችሁ?


በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


跟着我们:

广告


广告