መዝሙር 84:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አምላክ ሆይ፤ ጋሻችንን እይልን፤ የቀባኸውንም ተመልከት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጥ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አምላክ ሆይ! መርጠህ የቀባኸውን ንጉሣችንን ባርከው፤ ጋሻችን ስለ ሆነም ተመልከተው። 参见章节 |
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”