መዝሙር 58:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አምላክ ሆይ፤ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንበሶቹን መንጋጋ አወላልቅ! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 አምላክ ሆይ! የእነዚህን እንደ አንበሳ አስፈሪ የሆኑ ሰዎች ጥርስ ስበር፤ መንጋጋቸውንም አውልቅ። 参见章节 |
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።