Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 50:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በመከራ ጊዜ ወደ እኔ ጩኽ፤ አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 መከራ በሚደርስብህ ጊዜ ጥራኝ፤ እኔም አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”

参见章节 复制




መዝሙር 50:15
32 交叉引用  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ፊቱን ወደ ግድ​ግ​ዳው መልሶ እን​ዲህ ሲል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፦


እን​ዲ​ህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍ​ርድ ሰይፍ ወይም ቸነ​ፈር ወይም ራብ፥ ቢመ​ጣ​ብን በዚህ ቤት ፊትና በፊ​ትህ እን​ቆ​ማ​ለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመ​ከ​ራ​ች​ንም ወደ አንተ እን​ጮ​ኻ​ለን፥ አን​ተም ሰም​ተህ ታድ​ነ​ና​ለህ።


ወደ እር​ሱም ትጸ​ል​ያ​ለህ፥ እር​ሱም ይሰ​ማ​ሃል፤ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይሰ​ጠ​ሃል።


ዐይ​ኖቼን ወደ ተራ​ሮች አነ​ሣሁ፤ ረድ​ኤቴ ከወ​ዴት ይምጣ?


በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው።


በከ​ንቱ ያጠ​ፉኝ ዘንድ ወጥ​መ​ዳ​ቸ​ውን ሸሽ​ገ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ነፍ​ሴን በከ​ንቱ አበ​ሳ​ጭ​ተ​ዋ​ታ​ልና።


እና​ንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባ​ች​ሁን ታከ​ብ​ዳ​ላ​ችሁ? ከንቱ ነገ​ርን ለምን ትወ​ድ​ዳ​ላ​ችሁ? ሐሰ​ት​ንም ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?


አፌን በም​ሳሌ እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከቀ​ድሞ ጀምሮ ያለ​ው​ንም ምሳሌ እና​ገ​ራ​ለሁ።


የሰ​ማ​ነ​ው​ንና ያየ​ነ​ውን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የነ​ገ​ሩ​ንን፥ ለሚ​መጣ ትው​ልድ ከል​ጆ​ቻ​ቸው አል​ሰ​ወ​ሩም።


እና​ንተ ግን እንደ ሰው ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም እንደ አንዱ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ።


ሰው እና​ታ​ችን ጽዮን ይላል፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ሰው ተወ​ለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠ​ረ​ታት።


በአ​ንቺ የሚ​ኖሩ ሁሉ ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ ይና​ገ​ራሉ፥ በእ​ር​ሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።


በዚ​ያም ቀን አድ​ን​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው ሰዎች እጅ አል​ሰ​ጥ​ህም።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።


ፈራ፤ መላ​ል​ሶም ጸለየ፤ ላቡም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ደም ነጠ​ብ​ጣብ ሆነ።


ብዙ ፍሬ ብታ​ፈሩ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቴም ብት​ሆኑ በዚህ አባቴ ይከ​በ​ራል።


በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ጳው​ሎ​ስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በዜማ አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እስ​ረ​ኞ​ቹም ይሰ​ሙ​አ​ቸው ነበር።


ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።


ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የዚ​ያ​ችን የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ስን​ጥ​ቃት ከፈተ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ውኃ ወጣ፤ እር​ሱም ጠጣ፤ ነፍ​ሱም ተመ​ለ​ሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መን​ሰክ” ተብሎ ተጠራ።


跟着我们:

广告


广告