Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 47:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እን​ደ​ሰ​ማን እን​ዲሁ አየን፥ በሠ​ራ​ዊት ጌታ ከተማ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ከተማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሧል፤ እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፥ በጥበብ ዘምሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል፤ መንግሥታትንም የሚያስተዳድር እርሱ ነው።

参见章节 复制




መዝሙር 47:8
18 交叉引用  

ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታድ​ርግ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ” በሉ።


የአ​ሕ​ዛ​ብን ርስት ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለሕ​ዝቡ የሥ​ራ​ውን ብር​ታት አሳየ።


አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓ​ለም የም​ት​ኖ​ሩም ሁላ​ችሁ፥ አድ​ምጡ፤


በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን እን​ጠ​ግ​ባ​ለ​ንና፤ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ ደስ ይለ​ናል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


ፍር​ዴ​ንና በቀ​ሌን አድ​ር​ገ​ህ​ል​ኛ​ልና፤ የጽ​ድቅ ፈራጅ ሆይ፥ በዙ​ፋ​ንህ ላይ ተቀ​መ​ጥህ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተበ​ቃይ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ልጥ ተበ​ቃይ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ወ​ድዱ፥ ክፋ​ትን ጥሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ኑን ነፍ​ሶች ይጠ​ብ​ቃል፥ ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ ያድ​ና​ቸ​ዋል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ፥ የቀኙ ማዳን፥ የተ​ቀ​ደሰ ክን​ዱም ድንቅ ነውና።


በም​ድር ሁሉ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፥


በደ​ስ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፥ በሐ​ሤ​ትም ወደ ፊቱ ግቡ።


እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፣ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።


እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።


እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


跟着我们:

广告


广告