Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 42:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ቴ​ንም ደስ ወዳ​ሰ​ኛት ወደ አም​ላኬ እገ​ባ​ለሁ፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ በመ​ሰ​ንቆ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣ እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣ በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣ በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣ እንዴት ከሕዝቡ ጋራ እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዘወትር፦ አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤ በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ ልቤ በሐዘን ይሰበራል።

参见章节 复制




መዝሙር 42:4
28 交叉引用  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ር​ግጥ ያድ​ነ​ናል፤ ይህ​ች​ንም ከተማ የአ​ሦር ንጉሥ ሊይ​ዛት አይ​ች​ልም እያለ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ት​ታ​መኑ አያ​ድ​ር​ጋ​ችሁ።


ይህም መጥቼ ምድ​ራ​ች​ሁን ወደ​ም​ት​መ​ስ​ለው ምድር፥ እህ​ልና የወ​ይን ጠጅ፥ እን​ጀ​ራና ወይን፥ ወይ​ራና ማር ወዳ​ለ​ባት ምድር እስ​ካ​ፈ​ል​ሳ​ችሁ ድረስ በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም ነው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ና​ች​ኋል ብሎ ያታ​ል​ላ​ች​ኋ​ልና አት​ስ​ሙት።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ቀን ሕዝ​ቡን ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው አሰ​ና​በተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊ​ትና ለሰ​ሎ​ሞን፥ ለሕ​ዝ​ቡም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት በል​ባ​ቸው ደስ ብሎ​አ​ቸው ሄዱ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀኝ እንደ ነበ​ረው ጊዜ፥ ወደ ፊተ​ኛው ወራት ማን በመ​ለ​ሰኝ?


ጠማማ ልብም አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላ​ወ​ቅ​ሁም።


እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን አላ​ደ​ረ​ገ​ብ​ንም፥ እንደ በደ​ላ​ች​ንም አል​ከ​ፈ​ለ​ንም።


እኔም ከራሴ ጀምሮ፥ “ሰው ሁሉ ሐሰ​ተኛ ነው” አልሁ።


በሰ​ማይ የም​ት​ኖር ሆይ፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ንን ወደ አንተ አነ​ሣን።


ነፍሴ በኋ​ላህ ተከ​ታ​ተ​ለች፥ እኔ​ንም ቀኝህ ተቀ​በ​ለ​ችኝ።


ጥላዋ ተራ​ሮ​ችን ከደነ፥ ጫፎ​ች​ዋም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝግባ ሆኑ።


ጀር​ባ​ውን ከመ​ስ​ገ​ጃ​ቸው መለሰ፥ እጆ​ቹም በቅ​ር​ጫት ተገዙ።


በዐ​ልን እን​ደ​ሚ​ያ​ከ​ብሩ፥ ሁል​ጊዜ ደስ ሊላ​ችሁ፥ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ቦታ​የም ልት​ሄዱ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው በእ​ን​ቢ​ልታ ወደ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ልት​ሄዱ ይገ​ባ​ች​ኋል።


ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።


አሌፍ። ወርቁ እን​ዴት ደበሰ! ጥሩው ብር እን​ዴት ተለ​ወጠ! የከ​በ​ረው ዕንቍ በጎ​ዳ​ናው ሁሉ እን​ዴት ተበ​ተነ!


ሕዝቡ በሚ​ገ​ቡ​በት ጊዜ አለ​ቃው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይግባ፤ በሚ​ወ​ጡ​በ​ትም ጊዜ ይውጣ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ካህ​ናት በወ​ለ​ሉና በም​ሥ​ዋዑ መካ​ከል እያ​ለ​ቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕ​ዝ​ብህ ራራ፤ አሕ​ዛ​ብም ይገ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ርስ​ት​ህን ለማ​ላ​ገጫ አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል፦ አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።


እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።


አብ​ር​ሃም ግን እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕ​ይ​ወ​ትህ ተድ​ላና ደስታ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ በች​ጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እን​ዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድ​ላና ደስታ ያደ​ር​ጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀ​በ​ላ​ለህ።


አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያሉ መጻ​ተ​ኛና ድሃ-አደግ፥ መበ​ለ​ትም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በሚ​መ​ር​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


በሙላት ወጣሁ፥ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ፣ እግዚአብሔር አዋርዶኛልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና ኑኃሚን ለምን ትሉኛላችሁ? አለቻቸው።


跟着我们:

广告


广告