Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 39:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤ በከንቱም ይታወካል፤ ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነሆ፥ ዘመኖቼን ከእጅ መዳፍ አሳጠርካቸው፥ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሰው ከጥላም የተሻለ አይደለም፤ በከንቱ ይደክማል፤ ሀብትን ያከማቻል፤ ነገር ግን ማን እንደሚጠቀምበት አያውቅም።

参见章节 复制




መዝሙር 39:6
31 交叉引用  

“ከሴት የተ​ወ​ለደ ሟች ሰው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን ጥቂት ነው፥ የቍጣ መከ​ራ​ንም የተ​ሞላ ነው።


እን​ድ​ታ​ገሥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለ​ሁን? ሕይ​ወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ።


ሕይ​ወቴ እስ​ት​ን​ፋስ እንደ ሆነች አስብ፤ ዐይ​ኔም መል​ካም ነገ​ርን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ አታ​ይም።


የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።


የልጅ ልጆች ሥራ​ህን ያደ​ን​ቃሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይና​ገ​ራሉ፥


ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።


በእርሱ ላይ ዐይንህን ብታተኩር አታገኘውም፥ ለእርሱ የንስር ክንፍ ተዘጋጅቶለታልና። ወደሚቆምበትም ቤት ይመለሳልና።


ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ሕፃ​ን​ነ​ትና ጕብ​ዝና፥ አለ​ማ​ወ​ቅም ከንቱ ናቸ​ውና ከል​ብህ ቍጣን አርቅ፥ ከሰ​ው​ነ​ት​ህም ክፉ ነገ​ርን አስ​ወ​ግድ።


የነ​ገ​ሩን ሁሉ ፍጻሜ ስማ፤ ይህ የሰው ሁለ​ን​ተ​ናው ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቅ።


ሰባ​ኪው አለ፥ “ሁሉ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ነው።”


እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ብር​ንና ወር​ቅን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንና የአ​ው​ራ​ጆ​ችን መዝ​ገብ ለራሴ ሰበ​ሰ​ብሁ፤ ሴቶ​ችና ወን​ዶች አዝ​ማ​ሪ​ዎ​ችን፥ የሰ​ዎች ልጆ​ች​ንም ተድላ አደ​ረ​ግሁ፤ የወ​ይን ጠጅ ጠማ​ቂ​ዎ​ች​ንና አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም አበ​ዛሁ።


ያችም ባለ​ጠ​ግ​ነት በክፉ ንጥ​ቂያ ትጠ​ፋ​ለች፤ ልጅ​ንም ቢወ​ልድ በእጁ ምንም የለ​ውም።


ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።


ይህን ቀላ​ሉን የማ​ት​ችሉ ከሆነ በሌ​ላው ለምን ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ?


እና​ን​ተም የም​ት​በ​ሉ​ት​ንና የም​ት​ጠ​ጡ​ትን አት​ፈ​ልጉ፤ ወዲ​ያና ወዲ​ህም አት​በሉ፤ አት​ጨ​ነ​ቁ​ለ​ትም።


የበሉ እን​ዳ​ል​በሉ ይሆ​ናሉ፤ የጠ​ጡም እን​ዳ​ል​ጠጡ ይሆ​ናሉ፤ የዚህ ዓለም ተድላ ሁሉ ያል​ፋ​ልና።


ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።


ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጎአል፤ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላል። ለኋለኛው ቀን መዝገብን አከማችታችኋል።


“ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤


እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።


跟着我们:

广告


广告