መዝሙር 27:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እንደ ሥራቸውና እንደ ዐሳባቸው ክፋት ስጣቸው፤ እንደ እጃቸውም ሥራ ክፈላቸው፤ ፍዳቸውን በራሳቸው ላይ መልስ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣ በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው። 参见章节 |