መዝሙር 110:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ይከምራል፥ በሰፊ ምድር ላይ ራሶችን ይቀጠቅጣል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ የጦር ሜዳዎችንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፤ በምድር ላይ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ይደመስሳል። 参见章节 |
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”