Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 108:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በላዩ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ሹም፤ ሰይ​ጣ​ንም በቀኙ ይቁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣ በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስልንም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አቤቱ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የምትወደው ሕዝብህ ይድን ዘንድ፥ ጸሎታችንን ስማ፤ በኀይልህም ታደገን።

参见章节 复制




መዝሙር 108:6
22 交叉引用  

ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው።


እና​ን​ተም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈ​ጣ​ሪ​ዬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ፤ ሰም​ቶም በእ​ሳት የሚ​መ​ልስ አም​ላክ፥ እርሱ አም​ላክ ይሁን።” ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መል​ካም ነው” ብለው መለሱ።


የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ወይ​ፈ​ንም ወስ​ደው አዘ​ጋጁ፤ ከጥ​ዋ​ትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበ​ዓ​ልን ስም ጠሩ። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ የሠ​ሩ​ት​ንም መሠ​ዊያ እያ​ነ​ከሱ ይዞሩ ነበር።


እስከ ሠር​ክም ድረስ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር፤ ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስና የሚ​ያ​ደ​ም​ጥም አል​ነ​በ​ረም። ከዚ​ህም በኋላ መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ግ​በት ጊዜ ኤል​ያስ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲያ በቃ​ችሁ፤ ወግዱ፤ ሂዱም፥ እኔም መሥ​ዋ​ዕ​ቴን እሠ​ዋ​ለሁ” አላ​ቸው።


አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ም​ጠኝ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም ቸል አት​በ​ለኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥር​ሳ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው ውስጥ ይሰ​ብ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ን​በ​ሶ​ቹን መን​ጋ​ጋ​ቸ​ውን ያደ​ቅ​ቃል።


አቤቱ፥ ቀኝህ በኀ​ይል ከበረ፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላ​ቶ​ችን አደ​ቀቀ።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


በሮሜ ላላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዳ​ችሁ፥ ለመ​ረ​ጣ​ች​ሁና ላከ​በ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።


በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ።


ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤ በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መረ​ጣ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንና ወዳ​ጆች፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ርኅ​ራ​ኄን፥ ቸር​ነ​ት​ንና ትሕ​ት​ናን፥ የው​ሀ​ት​ንና ትዕ​ግ​ሥ​ትን ልበ​ሱት።


跟着我们:

广告


广告