Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 106:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ባረ​ካ​ቸ​ውም፥ እጅ​ግም በዙ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አላ​ሳ​ነ​ሰ​ባ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፣ ለከነዓን ጣዖታት የሠዉአቸውን፣ ንጹሕ ደም አፈሰሱ፤ ምድሪቱም በደም ተበከለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸን ደም፥ ለከነዓን ጣዖቶች የሠዉአቸውን ንጹሕ ደም አፈሰሱ፥ ምድርም በደም ረከሰች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 እነርሱ ለከነዓን ጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው ያቀረቡአቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በመግደል ንጹሕ ደም አፍስሰዋል፤ ምድሪቱም በደም ረከሰች።

参见章节 复制




መዝሙር 106:38
15 交叉引用  

ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።


ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።


ጻድ​ቁ​ንም ስለ ገደለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራራ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።


እጃ​ች​ሁን ወደ እኔ ብት​ዘ​ረጉ፥ ዐይ​ኖ​ችን ከእ​ና​ንተ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምህ​ላ​ንም ብታ​በዙ አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጆ​ቻ​ችሁ ደምን ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


ምድ​ርም በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ሰዎች ምክ​ን​ያት በደ​ለች፤ ሕጉን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ለው​ጠ​ዋ​ልና፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙ​ንም ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ከመ​ቅ​ደሱ መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ያመ​ጣል፤ ምድ​ርም ደም​ዋን ትገ​ል​ጣ​ለች፤ ሙታ​ኖ​ች​ዋ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ከ​ድ​ንም።


ትተ​ው​ኛ​ልና፥ ይህ​ንም ስፍራ እን​ግዳ አድ​ር​ገ​ው​ታ​ልና፥ እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ዐጥ​ነ​ዋ​ልና፥ የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ይህን ስፍራ በን​ጹ​ሓን ደም ሞል​ተ​ዋ​ልና፥


በእ​ጆ​ች​ሽም የን​ጹ​ሓን ድሆች ደም ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግ​ልጥ አገ​ኘ​ሁት እንጂ በጕ​ድ​ጓድ ፈልጌ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም።


ለእ​ኔም የወ​ለ​ድ​ሻ​ቸ​ውን ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ሽን ወስ​ደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ሠዋ​ሽ​ላ​ቸው፤ ገደ​ል​ሻ​ቸ​ውም።


እን​ዲ​ህም በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እን​ዲ​ደ​ርስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ደምን የም​ታ​ፈ​ስሺ፥ እን​ድ​ት​ረ​ክ​ሺም በራ​ስሽ ላይ ጣዖ​ታ​ትን የም​ታ​ደ​ርጊ ከተማ ሆይ!


“ምድር በአ​ሕ​ዛብ እንደ ተመ​ላች፥ ከተ​ማም በኀ​ጢ​አት ተመ​ል​ታ​ለ​ችና ሰን​ሰ​ለት ሥራ።


ከዘ​ር​ህም ለሞ​ሎክ አት​ስጥ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ስም አታ​ር​ክስ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ምድ​ሪ​ቱም ረከ​ሰች፤ ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ቷን በእ​ር​ስዋ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች ትተ​ፋ​ለች።


ምድ​ርን የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳት ደም ነውና የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን ምድር በነ​ፍስ ግድያ አታ​ር​ክ​ሷት። ምድ​ሪ​ቱም በደም አፍ​ሳሹ ደም ካል​ሆነ በቀር ከፈ​ሰ​ሰ​ባት ደም አት​ነ​ጻም።


አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ባደ​ረ​ግህ ጊዜ የን​ጹ​ሑን ደም በደል ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ታር​ቃ​ለህ።


跟着我们:

广告


广告