Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 21:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ክፉ ሰው ሲዋረድ የዋህ ሰው ዐዋቂ ይሆናል፤ ጥበብን የሚረዳ ሰውም ዕውቀትን ይቀበላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤ ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ፌዘኛ ቅጣትን በተቀበለ ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል፥ ጠቢብም ቢማር እውቀትን ይቀበላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ፌዘኛ በሚቀጣበት ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል፤ ለብልኅም ሰው ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ የበለጠ ዐዋቂ ይሆናል።

参见章节 复制




ምሳሌ 21:11
17 交叉引用  

ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።


ቀና ልብ ዕውቀትን ትፈልጋለች። የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።


ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥ ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።


የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥ የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።


ፌዘኛን ብትገርፈው አላዋቂው ብልሃተኛ ይሆናል፤ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው ግን ዕውቀትን ያገኛል።


ክፉዎችን የሚያስተምር ለራሱ ውርደትን ይቀበላል፥ ኃጥእንም የሚገሥጽ ራሱን ያዋርዳል።


ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል።


በዙ​ሪ​ያ​ቸው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከጩ​ኸ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ “ምድ​ሪቱ እን​ዳ​ት​ው​ጠን” ብለው ሸሹ።


ሐና​ን​ያም ይህን በሰማ ጊዜ ወድቆ ሞተ፤ ጽኑ ፍር​ሀ​ትም ሆነ፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ ፈሩ።


እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰም​ተው ይፍሩ፤ እን​ዲህ ያለ ክፉ ሥራም እን​ደ​ገና በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ደ​ገም።


የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታር​ቃ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሰም​ተው ይፈ​ራሉ።


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።


跟着我们:

广告


广告