Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የክፉዎች ዐይኖች ሁልጊዜ ክፋትን ይመለከታሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ሁልጊዜ ዝም ይላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የተጨቈኑ ሰዎች ዘመናቸው ሁሉ የከፋ ነው፤ በደስታ የተሞላ ልብ ግን የማይቋረጥ ፈንጠዝያ አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ልቡ የሚያዝን ሰው ዘመኑ ሁሉ የከፋች ናት፥ የልብ ደስታ ግን ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የጭቊን ኑሮ ዘወትር ጐስቋላ ነው፤ ደስተኞች ሰዎች ግን ዘወትር በኑሮአቸው ይረካሉ።

参见章节 复制




ምሳሌ 15:15
17 交叉引用  

ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።


ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።”


ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል፤ ልብ ሲያዝን ግን ፊት ይጠቍራል።


ቀና ልብ ዕውቀትን ትፈልጋለች። የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።


እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሀብት እግዚአብሔርን ባለመፍራት ከሚገኝ ብዙ መዝገብ ይሻላል።


በጎ ዐሳብ ገንዘብ ላደረጋት ሰው የሕይወት ምንጭ ናት፤ የሰነፎች ትምህርት ግን ክፉ ናት።


ደስ ያላት ልብ ፈውስን ታገኛለች፤ ኀዘንተኛ ሰው ግን አጥንቱን ያደርቃል።


በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ጳው​ሎ​ስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በዜማ አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እስ​ረ​ኞ​ቹም ይሰ​ሙ​አ​ቸው ነበር።


በተ​ስፋ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከራ ታገሡ፤ ለጸ​ሎት ትጉ።


በዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ርሱ ይቅ​ር​ታ​ውን ባገ​ኘ​ን​በት በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​መ​ካ​ለን እንጂ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


የክ​ር​ስ​ቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደ በዛ መጠን እን​ዲሁ መጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ይበ​ዛ​ልና።


ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።


ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።


跟着我们:

广告


广告