ምሳሌ 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ደግ ሴት ለባሏ ክብርን ታስገኛለች፥ ጽድቅን የምትጠላ ሴት ግን የውርደት ወንበር ናት። ሐኬተኞች ከብልጽግና ይደኸያሉ፥ ብርቱዎች ግን ብልጽግናን ይከተላሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ርኅሩኅ ሴት ክብር ታገኛለች፤ ጨካኝ ሰዎች ግን ብልጽግናን ብቻ ያገኛሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ሞገስ ያላት ሴት ክብርን ታገኛለች፥ ኃያላንም ሀብትን ያገኛሉ።። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ሞገስ ያላት ሴት ትከበራለች፤ መልካም ጠባይ የሌላት ሴት ግን ውርደት ያገኛታል። ሰነፍ ሰው ሀብት ማግኘት አይችልም፤ ታታሪ ሰው ግን ሀብታም ይሆናል። 参见章节 |