Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ፊልጵስዩስ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ይህ​ንም የምል ስለ አጣሁ አይ​ደ​ለም፤ ያለኝ እን​ደ​ሚ​በ​ቃኝ አው​ቃ​ለ​ሁና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይህን የምለው ስለ ቸገረኝ አይደለም፤ ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ይህን ስል ስለሚያስፈልገኝ ነገር እያማረርሁ አይደለም፤ ያለኝ ነገር ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ደግሞም ይህን የምለው ለኑሮዬ የሚያስፈልገኝን በማጣቴ አይደለም፤ እኔማ “ያለኝ ነገር ይበቃኛል” ማለትን ተምሬአለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።

参见章节 复制




ፊልጵስዩስ 4:11
13 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ ብሎ ስእ​ለት ተሳለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በም​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ ቢጠ​ብ​ቀኝ፥ የም​በ​ላ​ው​ንም እን​ጀራ፥ የም​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ልብስ ቢሰ​ጠኝ፥


ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀ​መጥ ወደደ፤ ልጁ​ንም ሲፓ​ራን ለሙሴ ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።


ጭፍ​ሮ​ችም መጥ​ተው፥ “እኛሳ ምን እና​ድ​ርግ?” አሉት፤ “በደ​መ​ወ​ዛ​ችሁ ኑሩ እንጂ በማ​ንም ግፍ አት​ሥሩ፤ ማን​ንም አት​ቀሙ፤ አት​በ​ድ​ሉም” አላ​ቸው።


በድ​ካ​ምና በጥ​ረት፥ ብዙ ጊዜም ዕን​ቅ​ልፍ በማ​ጣት፥ በመ​ራ​ብና በመ​ጠ​ማት፥ አብ​ዝ​ቶም በመ​ጾም፥ በብ​ር​ድና በመ​ራ​ቆት ተቸ​ገ​ርሁ።


ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ ሊያ​በ​ዛ​ላ​ችሁ ይች​ላል፤ ፍጹም በረ​ከ​ቱ​ንም ለዘ​ወ​ትር ያበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ ለሁ​ሉም ታተ​ር​ፉ​ታ​ላ​ችሁ፤ በጎ ሥራ መሥ​ራ​ት​ንም ታበ​ዛ​ላ​ችሁ።


ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።


በእ​ስ​ራ​ቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመ​ከራ ተባ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ የገ​ን​ዘ​ባ​ች​ሁ​ንም መዘ​ረፍ በደ​ስታ ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋል፤ በሰ​ማ​ያት ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ከዚህ የሚ​በ​ል​ጥና የተ​ሻለ ገን​ዘብ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


跟着我们:

广告


广告