Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ፊልጵስዩስ 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን እን​ድ​ል​ክ​ላ​ችሁ፥ እኔም ዜና​ች​ሁን ሰምቼ ደስ እን​ዲ​ለኝ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ስለ እናንተ ሰምቼ ደስ እንዲለኝ፣ ጢሞቴዎስን ቶሎ ወደ እናንተ ልልክላችሁ በጌታ ኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ነገር ግን ስለ እናንተ ባወቅሁ ጊዜ ደስ ተሰኝቼ እንድበረታታ ፈጥኜ ጢሞቴዎስን ልልክላችሁ በጌታ በኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እኔ ስለ እናንተ ሁኔታ በመስማት እንድጽናና ጢሞቴዎስን በፍጥነት ወደ እናንተ ለመላክ እንደሚያስችለኝ በጌታ ኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ነገር ግን ኑሮአችሁን ሳውቅ እኔ ደግሞ ደስ እንዲለኝ ፈጥኜ ጢሞቴዎስን ልልክላችሁ በጌታ በኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።

参见章节 复制




ፊልጵስዩስ 2:19
22 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በሰው የሚ​ታ​መን የሥጋ ክን​ዱ​ንም በእ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ደ​ግፍ፥ ልቡም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ርቅ ሰው ርጉም ነው።


አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።”


ወደ ደር​ቤ​ንና ወደ ልስ​ጥ​ራን ከተ​ማም ደረሰ፤ እነ​ሆም፥ በዚያ የአ​ን​ዲት ያመ​ነች አይ​ሁ​ዳ​ዊት ልጅ ጢሞ​ቴ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ አባቱ ግን አረ​ማዊ ነበረ።


ኢሳ​ይ​ያ​ስም ደግሞ እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “የእ​ሴይ ዘር ይነ​ሣል፤ ከእ​ርሱ የሚ​ነ​ሣ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ሕዝ​ቡም ተስፋ ያደ​ር​ጉ​ታል።”


ከእኔ ጋር በሥራ የሚ​ተ​ባ​በ​ረው ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ ከዘ​መ​ዶች ወገን የሚ​ሆኑ ሉቅ​ዮ​ስም፥ ኢያ​ሶ​ንም፥ ሱሲ ጴጥ​ሮ​ስም ሰላም ይሉ​አ​ች​ኋል።


ስለ​ዚ​ህም በየ​ስ​ፍ​ራው በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ የሄ​ድ​ሁ​በ​ትን መን​ገድ ይገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መ​ነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን ልኬ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እና​ን​ተም ልት​ድ​ኑ​በት የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን የእ​ው​ነት ቃል ሰም​ታ​ች​ሁና አም​ና​ችሁ፤ ተስፋ ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ታተ​ማ​ችሁ።


ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ባር​ያ​ዎች ከጳ​ው​ሎ​ስና ከጢ​ሞ​ቴ​ዎስ፥ በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ለሚ​ኖሩ፤ ከቀ​ሳ​ው​ስ​ትና ከዲ​ያ​ቆ​ናት ጋር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፤


እና​ን​ተም በእኔ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። ከእ​ኔም ጋር ሐሤት አድ​ርጉ።


እን​ድ​ታ​ዩ​ትና ደስ እን​ዲ​ላ​ችሁ፥ እኔም እን​ዳ​ላ​ዝን በቶሎ እል​ከ​ዋ​ለሁ።


ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤


ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


በዚህ ፈንታ “ጌታ ቢፈቅድ፥ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን፤” ማለት ይገባችኋል።


跟着我们:

广告


广告