Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አብድዩ 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የጭ​ፍ​ራ​ቸው ምርኮ የከ​ነ​ዓ​ንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራ​ጵታ ድረስ ይወ​ር​ሳል፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምር​ኮ​ኞች እስከ ኤፍ​ራታ ድረስ የደ​ቡ​ብን ከተ​ሞች ይወ​ር​ሳሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በከነዓን ያለው ይህ የእስራኤል ስደተኞች ወገን፣ እስከ ሰራፕታ ያለውን ምድር ይወርሳል፤ በሰፋራድም ያሉ የኢየሩሳሌም ስደተኞች፣ የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይህም የእስራኤል ልጆች የጦር ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፥ በስፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በስደት ላይ የነበሩት የሰሜን እስራኤል ሕዝብ ሖላ ከሚባል አገር ተመልሰው የከነዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ፤ በሰፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ስደተኞች በስተ ደቡብ ያሉትን ከተሞች ይይዛሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ይህም የእስራኤል ልጆች የጭፍራቸው ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፥ በስፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ።

参见章节 复制




አብድዩ 1:20
12 交叉引用  

የደ​ቡብ ከተ​ሞች ተዘ​ግ​ተ​ዋል፤ የሚ​ከ​ፍ​ታ​ቸ​ውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተሰ​ድ​ዶ​አል፤ ፈጽ​ሞም ተሰ​ድ​ዶ​አል።


በዚ​ያም ዘመን የይ​ሁዳ ቤት ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ይሄ​ዳል፤ በአ​ን​ድም ሆነው ከሰ​ሜን ምድር ርስት አድ​ርጌ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ሰጠ​ኋት ምድር ይመ​ጣሉ።


ምር​ኮ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና በብ​ን​ያም ሀገር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በደ​ጋ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ ሰዎች እር​ሻ​ውን በብር ይገ​ዛሉ፤ በው​ሉም ወረ​ቀት ፈር​መው ያት​ማሉ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ያቆ​ማሉ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በደ​ጋው ላይ ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ በብ​ን​ያ​ምም ሀገር፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በጎቹ በተ​ቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ያ​ቸው እጅ እንደ ገና ያል​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


እኔም ደግሞ በአ​ብ​ር​ሃ​ምና በይ​ስ​ሐቅ በያ​ዕ​ቆ​ብም ዘር ላይ ገዢ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እን​ዳ​ላ​ስ​ነሣ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘር እጥ​ላ​ለሁ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥ እም​ራ​ቸ​ው​ማ​ለ​ሁና።”


ሰዎ​ች​ንም፥ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ና​ንተ ላይ አበ​ዛ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ር​ሱ​አ​ች​ኋል፤ ርስ​ትም ትሆ​ኑ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ልጅ አልባ አታ​ደ​ር​ጓ​ቸ​ውም።


ኤል​ያስ የሲ​ዶና ክፍል በም​ት​ሆን በስ​ራ​ጵታ ወደ​ም​ት​ኖር ወደ አን​ዲት መበ​ለት ሴት እንጂ ከእ​ነ​ዚህ ወደ አን​ዲቱ እን​ኳን አል​ተ​ላ​ከም።


跟着我们:

广告


广告