Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አብድዩ 1:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ግ​ሮ​አ​ልና የያ​ዕ​ቆብ ቤት እሳት፥ የዮ​ሴ​ፍም ቤት ነበ​ል​ባል፥ የዔ​ሳ​ውም ቤት ገለባ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ው​ማል፤ ከዔ​ሳ​ውም ቤት ቅሬታ አይ​ኖ​ርም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የያዕቆብ ቤት እሳት፣ የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናል፤ ያቃጥሉታል፤ ይበሉትማል፤ ከዔሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም።” እግዚአብሔር ተናግሯል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታ ተናግሮአልና የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባልም፥ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናሉ፥ እነርሱንም ያቃጥሉአቸዋል ይበሉአቸውማል፥ ከዔሳውም ቤት የሚተርፍ አይኖርም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የያዕቆብ ልጆች እንደ እሳት፥ የዮሴፍ ልጆች እንደ ነበልባል፥ የዔሳውም ልጆች እንደ ገለባ ይሆናሉ፤ እሳት ገለባን እንደሚያቃጥል የያዕቆብና የዮሴፍ ልጆች የዔሳውን ልጆች ያጠፋሉ። ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም ተናግሮአልና የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባልም፥ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናሉ፥ እነርሱንም ያቃጥሉአቸዋል ይበሉአቸውማል፥ ከዔሳውም ቤት ቅሬታ የለውም።

参见章节 复制




አብድዩ 1:18
23 交叉引用  

እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በደ​ለኛ እንደ ሆንሁ አው​ቄ​አ​ለ​ሁና እነሆ፥ ከዮ​ሴፍ ቤት ሁሉ አስ​ቀ​ድሜ ዛሬ መጣሁ፤ ጌታ​ዬ​ንም ንጉ​ሡን ልቀ​በል ወረ​ድሁ።”


ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ብር​ሃን እንደ እሳት ይሆ​ናል፤ በሚ​ነ​ድድ እሳ​ትም ይቀ​ድ​ሰ​ዋል፤ ዛፉ​ንም እንደ ሣር ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ከነ​በ​ል​ባል ኀይል አያ​ድ​ኑም፤ እንደ እሳ​ትም ፍም ይሆ​ኑ​ብ​ሻል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።


ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


ኀጢ​አት እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ እሳት እንደ በላ​ችው ደረቅ ሣር ይቃ​ጠ​ላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃ​ጠ​ላል፤ በተ​ራ​ራ​ዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃ​ጠ​ላል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ምድር ሁሉ ትቃ​ጠ​ላ​ለች፤ ሕዝ​ቡም እሳት እን​ደ​ሚ​በ​ላው እን​ጨት ሆኖ​አል፤ ሰውም ለወ​ን​ድሙ አይ​ራ​ራም።


በም​ጐ​በ​ኛ​ቸ​ውም ዓመት በዓ​ና​ቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ማንም ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ተ​ርፍ የለም።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ውሰ​ድና፦ ይሁ​ዳ​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች በላዩ ጻፍ፤ ሌላም በትር ውሰ​ድና፦ የኤ​ፍ​ሬም በትር ለዮ​ሴ​ፍና ለባ​ል​ን​ጀ​ሮቹ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ብለህ በላዩ ጻፍ።


እነሆ በኤ​ፍ​ሬም እጅ ያለ​ውን የዮ​ሴ​ፍን በትር ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ከይ​ሁዳ በትር ጋር አጋ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አንድ በት​ርም አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ጄም ውስጥ አንድ ይሆ​ናሉ በላ​ቸው።


ድም​ፃ​ቸ​ውም በተ​ራራ ላይ እንደ አሉ ሠረ​ገ​ሎች ድምፅ፥ ገለ​ባ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​በላ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ድምፅ ነው፤ ለሰ​ል​ፍም እንደ ተዘ​ጋጀ እንደ ብዙና ብርቱ ሠራ​ዊት ያኰ​በ​ኵ​ባሉ።


የአ​ዛ​ጦን ነዋ​ሪ​ዎ​ችን አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም ሕዝብ ይጠ​ፋ​ለሁ፤ እጄ​ንም በአ​ቃ​ሮን ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የቀ​ሩ​ትም ይጠ​ፋሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል።


በጽዋ የቀላ ወይን ለሚ​ጠጡ፥ እጅግ በአ​ማረ ሽቱም ለሚ​ቀቡ፥ በዮ​ሴፍ ስብ​ራት ለማ​ያ​ስቡ ወዮ​ላ​ቸው።


በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ ላይ እንደ ጠጣህ እን​ዲሁ አሕ​ዛብ ሁሉ ወይ​ንን ይጠ​ጣሉ፤ አዎን፥ ይጠ​ጣሉ፥ ይጨ​ል​ጡ​ማል፤ እን​ዳ​ል​ነ​በ​ሩም ይሆ​ናሉ።


በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።


እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በዚህ መሠ​ረት ላይ በወ​ር​ቅና በብር፥ በከ​በረ ድን​ጋ​ይና በእ​ን​ጨት፥ በሣ​ርና በአ​ገዳ የሚ​ያ​ንጽ ቢኖ​ርም፥


跟着我们:

广告


广告