Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ርኵ​ሰት የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ሰዎች መጡ፤ ስለ​ዚ​ህም በዚያ ቀን ፋሲ​ካን ያደ​ርጉ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አንዳንዶቹ ግን የሰው ሬሳ በመንካታቸው በሥርዐቱ መሠረት ረክሰው ስለ ነበር በዚያ ዕለት የፋሲካን በዓል ማክበር አልቻሉም፤ ስለዚህም በዚያ ዕለት ወደ ሙሴና ወደ አሮን መጥተው፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሞተ ሰው ሬሳን በመንካት የረከሱ ሰዎችም ነበሩ፥ ስለዚህም በዚያ ቀን የፋሲካን በዓል ለማክበር አልቻሉም ነበር። በዚያም ቀን በሙሴና በአሮን ፊት ቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ነገር ግን በድን ከመንካታቸው የተነሣ ያልነጹ ጥቂት ሰዎች ስለ ነበሩ በዚያን ቀን የፋሲካን በዓል ማክበር አልቻሉም፤ ስለዚህ እነርሱ ወደ ሙሴና አሮን ዘንድ ቀርበው እንዲህ አሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በሞተ ሰው ሬሳ የረከሱ ሰዎችም ነበሩ፥ ስለዚህም በዚያ ቀን ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ አልቻሉም። በዚያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ።

参见章节 复制




ዘኍል 9:6
16 交叉引用  

ሙሴም አማ​ቱን፥ “ሕዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ ለመ​ጠ​የቅ ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤


አሁ​ንም እመ​ክ​ር​ሃ​ለ​ሁና ስማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለሕ​ዝቡ ሁን፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ርስ፤


በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሁል​ጊዜ ፈረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ው​ንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ ግን እነ​ርሱ ፈረዱ።


ወደ ሞተ ሰው ሁሉ አይ​ግባ፤ በአ​ባ​ቱም ወይም በእ​ናቱ አይ​ር​ከስ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ቱም ሴት ልጅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠርቶ ሰደበ፤ ወደ ሙሴም አመ​ጡት። እና​ቱም ከዳን ነገድ የዳ​ቤር ልጅ ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ሰሎ​ሚት ነበረ።


በሰ​ን​በት ቀን ዕን​ጨት ሲለ​ቅም ያገ​ኙ​ትም ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ አመ​ጡት።


“የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


“ሰው በቤት ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ቤት የሚ​ገባ ሁሉ በቤ​ቱም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


ንጹ​ሕም ሰው ሂሶ​ጱን ወስዶ በው​ኃው ውስጥ ያጠ​ል​ቀ​ዋል፤ በቤ​ቱም፥ በዕ​ቃ​ውም ሁሉ፥ በዚ​ያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥ​ን​ቱ​ንም ወይም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን፥ ወይም የሞ​ተ​ውን፥ ወይም መቃ​ብ​ሩን በነ​ካው ላይ ይረ​ጨ​ዋል።


በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በአ​ለ​ቆ​ቹም፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት ቆመው እን​ዲህ አሉ፦


በአ​ባ​ታ​ችን ወን​ድ​ሞች መካ​ከል ርስ​ትን ስጠን።” ሙሴም ነገ​ራ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረበ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለም​ጻ​ሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገ​ርም ያለ​በ​ትን ሁሉ በሰ​ው​ነቱ የረ​ከ​ሰ​ውን ሁሉ ከሰ​ፈሩ እን​ዲ​ያ​ወጡ እዘ​ዛ​ቸው፤


በዚ​ያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ። እነ​ዚ​ያም ሰዎች “እኛ በሰ​ው​ነ​ታ​ችን ርኵ​ሰት ያለ​ብን ሰዎች ነን፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በጊ​ዜው ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ና​ቀ​ርብ ስለ ምን እን​ከ​ለ​ከ​ላ​ለን?” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።


跟着我们:

广告


广告