Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 8:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ስጦታ አድ​ርጌ አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ልዩ በሆ​ነች ድን​ኳን ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ኀጢ​አት ያቃ​ልሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ተሰጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ መቅ​ደስ የሚ​ቀ​ርብ አይ​ኑር።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እስራኤላውያንን ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት እንዲያከናውኑና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ ቢቀርቡ እንዳይቀሠፉ ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፣ ከእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ሌዋውያኑን ስጦታ አድርጌ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች እንዲያስተስርዩላቸው፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲሠሩ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ።

参见章节 复制




ዘኍል 8:19
12 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘዘ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ነገር ግን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በዕ​ቃ​ዎ​ችዋ ሁሉ፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋ​ው​ያ​ንን አቁ​ማ​ቸው። ድን​ኳ​ን​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​አ​ትም፤ በድ​ን​ኳ​ን​ዋም ዙሪያ ይስ​ፈሩ።


ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ዕዳ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስ​ፈሩ፤ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ።”


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ጥና​ህን ውሰድ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ እሳት አድ​ር​ግ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨም​ር​በት፤ ወደ ማኅ​በ​ሩም ፈጥ​ነህ ውሰ​ደው፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍጣ ወጥ​ቶ​አ​ልና፥ ሕዝ​ቡ​ንም ያጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ጀም​ሮ​አል” አለው።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወስ​ጄ​አ​ለሁ።


ሙሴና አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲሁ በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው።


የኢ​ያ​ኮ​ንዩ ልጆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመ​ል​ክ​ተው ከቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ጋር አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሕ​ዝቡ አም​ስት ሺህ ሰባ ሰዎ​ችን መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን በታ​ላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለ​ቀሱ።


跟着我们:

广告


广告