ዘኍል 7:86 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)86 ዕጣንም የተሞሉ ዐሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፥ እያንዳንዱ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ዐሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭልፋዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሃያ ሰቅል ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም86 ዕጣን የሞላባቸው ዐሥራ ሁለቱ የወርቅ ጭልፋዎችም እያንዳንዳቸው በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ሰቅል መዘኑ፤ በአጠቃላይ የወርቅ ጭልፋዎቹ ክብደት አንድ መቶ ሃያ ሰቅል ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)86 ዕጣንም የተሞሉት ዐሥራ ሁለቱ የወርቅ ሙዳዮች፥ እያንዳንዳቸው በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ሰቅል ነበሩ፤ የሙዳዮቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሀያ ሰቅል ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም86 ዐሥራ ሁለቱ ከወርቅ የተሠሩት የዕጣን ማስቀመጫዎች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት እያንዳንዳቸው ዐሥር ሰቅል የሚመዝኑ ሲሆኑ በጠቅላላው አንድ መቶ ኻያ ሰቅል ይመዝኑ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)86 ዕጣንም የተሞሉ አሥራ ሁለቱ የወርቅ ጭልፋዎች፥ እያንዳንዱ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን አሥር አሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭልፋዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሀያ ሰቅል ነበረ። 参见章节 |