Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 መሠዊያው በተቀባበት ቀን አለቆች የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ ስጦታዎችን አመጡ፤ በመሠዊያውም ፊት አቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቁርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 መሠዊያው በተባረከበት ቀን መሪዎቹ መሠዊያውን ለመቀደስ በመሠዊያው ፊት ቊርባን አቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቍርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።

参见章节 复制




ዘኍል 7:10
12 交叉引用  

ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰላም መሥ​ዋ​ዕት ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን አቀ​ረበ። ንጉ​ሡና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቀደሱ፤ አከ​በ​ሩም።


በዚ​ያ​ችም ዕለት ንጉሡ ሰሎ​ሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን ሠዋ። እን​ዲሁ ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ አከ​በሩ።


መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀድሶ፥ ሰባት ቀን በዓል አድ​ርጎ ነበ​ርና በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የፍ​ጻሜ በዓል አደ​ረገ።


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር በተ​መ​ረቀ ጊዜ ምረ​ቃ​ውን በደ​ስ​ታና በም​ስ​ጋና፥ በመ​ዝ​ሙ​ርም፥ በጸ​ና​ጽ​ልም፥ በበ​ገ​ናም፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ለማ​ድ​ረግ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ኑን በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ሁሉ ፈለጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ደስታ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ደስም አላ​ቸው፤ ሴቶ​ቹና ልጆ​ቹም ደግሞ ደስ አላ​ቸው፤ ደስ​ታ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሩቅ ተሰማ።


አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አል​ፈር፤ በጽ​ድ​ቅ​ህም አስ​ጥ​ለኝ፥ አድ​ነ​ኝም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ በየ​ቀኑ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ መባ​ውን በቀን በቀኑ ያቅ​ርብ” አለው።


መሠ​ዊ​ያው በተ​ቀባ ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ለመ​ሠ​ዊ​ያው መቀ​ደሻ ያቀ​ረ​ቡት መባ ይህ ነበረ፤ ዐሥራ ሁለት የብር ወጭ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የብር ድስ​ቶች፥ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፤


የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደ​ሮች፥ ስድ​ሳም አውራ በጎች፥ ስድ​ሳም አውራ ፍየ​ሎች፥ ስድ​ሳም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ። መሠ​ዊ​ያው ከተ​ቀባ በኋላ ለመ​ቀ​ደ​ሻው የቀ​ረበ ቍር​ባን ይህ ነበረ።


ጸሐ​ፍ​ትም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላ​ስ​መ​ረቀ ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ስ​መ​ር​ቀው ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።


跟着我们:

广告


广告