Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ዕቃ​ውን ሁሉ፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ መክ​ደ​ኛ​ዎ​ቹ​ንም፥ ያመድ ማፍ​ሰ​ሻ​ዎ​ቹን፥ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ያስ​ቀ​ም​ጡ​በት፤ በእ​ር​ሱም የአ​ቆ​ስ​ጣን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይዘ​ርጉ፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ወስ​ደው ማስ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንና ማስ​ቀ​መ​ጫ​ውን ይሸ​ፍ​ኑት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣው ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስ​ጥም አድ​ር​ገው በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ዎቹ ላይ ያኑ​ሩት፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም ለመሠዊያው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች በሙሉ፣ የእሳት ማንደጃዎቹን፣ ሜንጦዎቹን፣ የእሳት መጫሪያዎቹንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን በላዩ ላይ ያድርጉ፤ በእነዚህም ላይ የአቆስጣ ቍርበት መሸፈኛ አልብሰው መሎጊያዎቹን በየቦታቸው ያስገቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቅሙትን ዕቃዎች፥ ማለትም ማንደጃዎችን፥ ሜንጦዎችን፥ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ያስቀምጡበት፤ የተለፋውንም ስስ ቊርበት በላዩ ደርበው መሎጊያዎችን ያስገቡበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ድስቶቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።

参见章节 复制




ዘኍል 4:14
7 交叉引用  

ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ሁሉ፥ የወ​ር​ቁ​ንም መሠ​ዊያ፥ ኅብ​ስተ ገጽ የነ​በ​ረ​ባ​ቸ​ውን ገበ​ታ​ዎች ሠራ።


“ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ይሁን፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ይሁን።


ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።


አመ​ዱ​ንም ያስ​ወ​ግዱ፤ መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያድ​ርጉ፤ ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


በላ​ዩም የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ያድ​ር​ጉ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በላይ ሁለ​ን​ተ​ናው ሰማ​ያዊ የሆነ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ያግ​ቡ​በት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግ​ቡ​በት።


跟着我们:

广告


广告