Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 32:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሙሴም፥ “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች ሁላ​ቸው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለጦ​ር​ነት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገሩ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ድል ብት​ነሡ ፥ የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እንዲህም አላቸው፤ “የጋድና የሮቤል ወንድ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ለጦርነት በመዘጋጀት በእግዚአብሔር ፊት ከእናንተ ጋራ ዮርዳኖስን የሚሻገር ከሆነ፣ ምድሪቱም በእጃችሁ ስትገባ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ስጧቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ለጦርነት የተዘገጋጁት የጋድና የሮቤል ልጆች ሁሉ ከእናንተ ጋር በጌታ ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “የጋድና የሮቤል ሰዎች ዮርዳኖስን ተሻግረው በእግዚአብሔር መሪነት ለጦርነት የሚዘጋጁ ከሆነና በእነርሱም ርዳታ ምድሪቱን የምትወርሱ ከሆነ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርጋችሁ ስጡአቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ሙሴም፦ የጋድና የሮቤል ልጆች ሁላቸው ጋሻ ጦራቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ።

参见章节 复制




ዘኍል 32:29
10 交叉引用  

እኛ ግን ለጦ​ር​ነት ታጥ​ቀን ወደ ስፍ​ራ​ቸው እስ​ክ​ና​ገ​ባ​ቸው ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆ​ቻ​ችን በተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ።


ሙሴም ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን፥ የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ነገድ አባ​ቶች አለ​ቆች አዘ​ዛ​ቸው።


የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ባይ​ሻ​ገሩ ግን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ችሁ ወደ ከነ​ዓን ምድር ንዱ​አ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ና​ንተ መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ” አላ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ ርስት አድ​ርጎ ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለጋ​ድም ልጆች፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው።


ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥


ለሁ​ለቱ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው ነገድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”


የሮ​ቤ​ልም ልጆች የጋ​ድም ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሄዱ፤ በሙ​ሴም እጅ በተ​ሰጠ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ተቀ​በ​ሉት ወደ ርስ​ታ​ቸው ወደ ገለ​ዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከ​ነ​ዓን ምድር ካለ​ችው ከሴሎ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ተመ​ለሱ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ ገለ​ዓ​ዳ​ዊዉ ኢያ​ዕር ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሃያ ሁለት ዓመት ገዛ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ታላ​ቂቱ ልጄ ሜሮብ እነ​ኋት፤ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁን​ልኝ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጦር​ነት ተጋ​ደል” አለው። ሳኦ​ልም፥ “የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በእ​ርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእ​ርሱ ላይ አት​ሁን” ይል ነበር።


跟着我们:

广告


广告