Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 31:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ሙሴ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ድርሻ ከሰ​ውና ከእ​ን​ስሳ ከሃ​ምሳ አንድ ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ሌዋ​ው​ያን ሰጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ላይ፣ ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከየዐምሳው ሰውና እንስሳ አንዳንድ መርጦ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጣቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከኀምሳ አንድ ወሰደ፥ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው የጌታን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ከዚህም ድርሻ ሙሴ ከኀምሳው አንድ እስረኛ፥ ከኀምሳው አንድ እንስሳ ወስዶ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር ድንኳን ላይ ኀላፊነት ላላቸው ለሌዋውያን ሰጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከአምሳ አንድ ወሰደ፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ።

参见章节 复制




ዘኍል 31:47
12 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ፤ እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ዕዳ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስ​ፈሩ፤ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ።”


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ድርሻ እኩ​ሌታ፥ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከእ​ን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ ከአ​ምሳ አንድ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ለሌ​ዋ​ው​ያን ትሰ​ጣ​ለህ።”


ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።


በሠ​ራ​ዊት አእ​ላ​ፋት ላይ የተ​ሾ​ሙት አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች ወደ ሙሴ ቀረቡ፤ ሙሴ​ንም እን​ዲህ አሉት፦


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


跟着我们:

广告


广告