ዘኍል 31:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 የማረኩትን ምርኮውንና የዘረፉትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ እስራኤልም ልጆች፥ በዮርዳኖስም አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር አመጡ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 የማረኳቸውን ሰዎች፣ የነዷቸውን እንስሳትና የዘረፉትን ሀብት በሙሉ፣ ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ፣ በሞዓብ ወዳለው፣ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር እንዲሁም መላው የእስራኤላውያን ማኅበር ወዳሉበት ሰፈራቸው አመጧቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን፥ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር፥ ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር አመጡ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ከዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ትይዩ በሞአብ ሜዳ ላይ ሰፍረው ወደነበሩት ወደ ሙሴና ወደ አልዓዛር እንዲሁም ወደ መላው ማኅበር አመጡአቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር፥ በዮርዳኖስም አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር አመጡ። 参见章节 |