Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 29:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 “እነ​ዚ​ህ​ንም፥ ከስ​እ​ለ​ታ​ች​ሁና በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ ከም​ታ​መ​ጡት ሌላ፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ህ​ልም፥ ለመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ በበ​ዓ​ላ​ችሁ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “ ‘ከስእለትና ከበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቍርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቍርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በበዓላታችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 “እነዚህንም፥ ከስእለታችሁና በፈቃዳችሁ ከምታመጡት ቁርባን ሌላ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእህልም ለመጠጥም ቁርባን፥ ለአንድነትም መሥዋዕታችሁ በበዓላችሁ ጊዜ ለጌታ አቅርቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “በተወሰኑላችሁ በዓሎች እነዚህን ለጌታ ታቀርባላችሁ፤ ይህም ከስእለት ቊርባናችሁ፥ በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት መባ ሌላ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን፥ የእህል ቊርባናችሁን፥ የመጠጥ ቊርባናችሁንና የአንድነት ቊርባናችሁን ታቀርባላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 እነዚህንም፥ ከስእለታችሁና በፈቃዳችሁ ከምታመጡት ሌላ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእህልም ለመጠጥም ቍርባን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕታችሁ በበዓላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

参见章节 复制




ዘኍል 29:39
20 交叉引用  

በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም እንደ ሥር​ዐቱ ቍጥር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘወ​ትር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ ለማ​ቅ​ረብ፥


የሌ​ዋ​ዊ​ውም የይ​ም​ላእ ልጅ የም​ሥ​ራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባና የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን ነገ​ሮች እን​ዲ​ያ​ካ​ፍል ሕዝቡ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ቀ​ረ​ቡት ላይ ተሾመ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥ​ዋ​ትና በማታ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በበ​ዓ​ላ​ትም ለሚ​ቀ​ር​በው ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ንጉሡ ከገ​ን​ዘቡ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ወሰነ።


እንደ ተጻ​ፈ​ውም የዳስ በዓል አደ​ረጉ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም ለየ​ዕ​ለቱ የተ​ገ​ባ​ውን የየ​ዕ​ለ​ቱን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቍ​ጥር አቀ​ረቡ።


ከዚ​ያም በኋላ ዘወ​ትር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የመ​ባ​ቻ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ት​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት፥ ሰውም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የሰ​ጠ​ውን ቍር​ባን አቀ​ረቡ።


ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት፥ ስለ ኅብ​ስተ ገጽም፥ ዘወ​ት​ርም በሰ​ን​በ​ትና በመ​ባቻ ስለ ማቅ​ረብ ስለ እህሉ ቍር​ባ​ንና ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ ስለ በዓ​ላ​ትም፥ ስለ ተቀ​ደ​ሱ​ትም ነገ​ሮች፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስለ​ሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥


መባ​ቻ​ች​ሁ​ንና በዓ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ነፍሴ ጠል​ታ​ለች፤ አስ​ጸ​ያፊ ሆና​ች​ሁ​ብ​ኛል፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁ​ንም ይቅር አል​ልም።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ቅዱ​ሳት ጉባ​ኤ​ያት ብላ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሩ​አ​ቸው በዓ​ላቴ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት እነ​ዚህ ናቸው።


በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እና​ንተ ማስ​ተ​ስ​ረያ ትሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናትና በዚ​ያች ቀን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።


እነ​ዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ታት ሌላ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ት​ሰ​ጡት ከስ​ጦ​ታ​ችሁ ሌላ፥ ከስ​እ​ለ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ከም​ታ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ና​ች​ሁን ብታ​ቀ​ር​ቡ​ል​ኝም እንኳ አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም አል​መ​ለ​ከ​ትም።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ ቍር​ባ​ኔን፥ መባ​ዬ​ንና የበጎ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ቴን በበ​ዓ​ላት ቀኖች ታቀ​ር​ቡ​ልኝ ዘንድ ጠብቁ።


ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።


ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።


“ስእ​ለ​ቱን የተ​ሳ​ለው የባ​ለ​ስ​እ​ለቱ፥ እጁም ከሚ​ያ​ገ​ኘው ሌላ ስለ ስእ​ለቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በው የቍ​ር​ባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእ​ለ​ቱን እንደ ተሳለ እንደ ስእ​ለቱ ሕግ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።”


ብት​በ​ሉም፥ ብት​ጠ​ጡም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አድ​ር​ጉት።


ወደ​ዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ ስዕ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ የላ​ማ​ች​ሁ​ንና የበ​ጋ​ች​ሁ​ንም በኵ​ራት ውሰዱ።


跟着我们:

广告


广告