Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 29:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ዐሥራ አም​ስ​ተ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ሰባት ቀንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል አድ​ርጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም የሰባት ቀን በዓል አክብሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በሰባተኛውም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለጌታ በዓል አድርጋችሁ ታከብራላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን በአንድነት ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ ይህንንም በዓል ለእግዚአብሔር ክብር በመስጠት ሰባት ቀን አክብሩ፤ በዚህም ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከሰባተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ።

参见章节 复制




ዘኍል 29:12
16 交叉引用  

ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በይ​ሁዳ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ በዓል ያለ በዓል አደ​ረገ፤ ለሠ​ራ​ቸ​ውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ በቤ​ቴል ወደ ሠራው መሠ​ዊያ ወጣ፤ ለኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችም የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን ካህ​ናት በቤ​ቴል አኖ​ራ​ቸው።


እንደ ተጻ​ፈ​ውም የዳስ በዓል አደ​ረጉ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም ለየ​ዕ​ለቱ የተ​ገ​ባ​ውን የየ​ዕ​ለ​ቱን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቍ​ጥር አቀ​ረቡ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ባለው በዓል የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በዳስ ይቀ​መጡ ዘንድ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ይና​ገ​ሩና ያውጁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።


ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨ​ረ​ሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ ያነ​ብብ ነበር። በዓ​ሉ​ንም ሰባት ቀን ያህል አደ​ረጉ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እንደ ሕጋ​ቸው ወጡ።


በፊቴ ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። በእ​ር​ሻም የም​ት​ዘ​ራ​ትን የፍ​ሬ​ህን በኵ​ራት የመ​ከር በዓል፥ ዓመ​ቱም ሲያ​ልቅ ፍሬ​ህን ከእ​ርሻ ባከ​ማ​ቸህ ጊዜ የመ​ክ​ተ​ቻ​ውን በዓል ጠብቅ።


የሰ​ባ​ቱ​ንም ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እር​ሱም የስ​ንዴ መከር መጀ​መ​ሪያ ነው፤ በዓ​መ​ቱም መካ​ከል የመ​ክ​ተቻ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በበ​ዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን ከዘ​ይቱ ጋር እን​ዲሁ ያቅ​ርብ።”


መጀ​መ​ሪ​ያ​ይቱ ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።


“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወሩ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ለእ​ና​ንተ ይህች ዕለት የተ​ቀ​ደ​ሰች ናት፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ምል​ክት ያለ​ባት ቀን ትሁ​ን​ላ​ችሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ዐሥራ ሦስት በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች አቅ​ርቡ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁኑ።


“ስም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን የተ​ቀ​ደሰ በዓል ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


跟着我们:

广告


广告