Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጠቦት ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እንደዚሁም ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋራ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አቅርቡ፤ ይህም ለሚቃጠል መሥዋዕት ሲሆን ሽታው ደስ የሚያሰኝና በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋር በዘይት የተለወሰ የእህል ቊርባን አንድ ኪሎ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ ይህም የሚቃጠል መሥዋዕት ሁሉ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ መባ ሆኖ ይቀርባል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት ታቀርባላችሁ።

参见章节 复制




ዘኍል 28:13
4 交叉引用  

ከአ​ንዱ ጠቦ​ትም ጋር የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ለአ​ን​ዱም አውራ በግ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ወይም መሥ​ዋ​ዕት ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታዘ​ጋ​ጃ​ላ​ችሁ።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወይ​ፈን ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለአ​ው​ራው በግ ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥


የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ለአ​ንድ ወይ​ፈን የኢን ግማሽ፥ ለአ​ው​ራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአ​ን​ዱም ጠቦት የኢን አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ይሆ​ናል፤ ይህ ለዓ​መቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


跟着我们:

广告


广告